የኮንሶ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ቀንን በማሰብ ‹‹ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም!›› በሚል መሪ-ቃል ውይይት አካሄደ፡፡

ኤች አይ ቪ/ኤድስ በሽታን በመከላከል ምርታማና ጤነኛ እሳቤ ያለው ትውልድ መገንባት እንደሚያስፈልግ የመምሪያው ባለሙያዎች መክረውበታል።

የነገ ታሪክ እንዳይደበዝዝ የትናንት ስህተትን በማረምና

በመተባበር ሰብዓዊ መብትን ያከበረ አገልግሎት ማስፋት እንደሚያስፈልግም ሃሳባቸውን በጋራ አብላልተውታል፡፡

“በቃ!” በማለት፣ ብሎም በመተባበር ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት ሃላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉም ቃል ገብተዋል።

የምሪያው ሰራተኞች በሙሉ በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ አገልግሎቱን በብቃትና በስፋት ተደራሽ ለማድረግ የበኩላቸውን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩም መምሪያው ‹‹ሙስናን የሚፀየፍ ትውልድ ለብልጽግናችን!›› በሚል መሪ-ቃል በስነምግባሩ ያበበ ትውልድ መገንባት እንደሚገባ ጨምረው ተወያይተዋል።

ሙስና የልማት እንዳይፈጥን የሚያደርግ ደንቃራ ተግባር ነው ያሉት የመምሪያው ሠራተኞች፣ ከመርሃ-ግብሩ በላይ ለስኬቱ መስራት እንደሚገባ ዕለቱን በማሰብ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በኮንሶ ‹‹ኾራታ›› የሚባል ባህላዊ የቅጣት ማስተማሪያና የገንዘብ አሰባሰብ ስርዓት ጥንት በኮንሶ ማህበረሰብ የነበረ ሲሆን የ‹‹ኾራታ››ን ገንዘብ በመቀበል አመራሩ ሁኔታዎች ውሳኔ እስኪያገኙ ድረስ ለማንኛውም ልማትና ለግል ሥራ አለማዋሉ አንዱ የሙስና መከላከያ መንገድ በመሆኑ የኮንሶ ታሪክ ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ሙስና ሃገረራዊ ዕድገትን የሚገታ፣ ትውልድን የሚያቀጭጭ፣ ህሊናንን የሚያቆሽሽ፣ ወገንን የሚጎዳና ለውድቀት ጉድጓድ የሚምስ ፀያፊ ተግባር በመሆኑ ከራሳችን አልፈን ለትውልድና ለሃገር ዕድገት በትኩረትና በዕውቀት ልንሠራ ይገባልም ብለዋል፡፡

መረጃው

የኮንሶ ዞን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

ህዳር 20/2016 ዓ.ም