5ኛዉ ዙር ዞን አቀፍ የተቀናጀ የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በካራት ዙሪያ ወረዳ በመጨሎ ቀበሌ

ዞን አቀፍ የተቀናጀ ፖሊዮ ክትባት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ በመጨሎ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ።

5ኛዉ ዙር ዞን አቀፍ የተቀናጀ የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በካራት ዙሪያ ወረዳ በመጨሎ ቀበሌ የዞንና የወረዳው ጤና ኃላፊዎች በተገኙበት መሰጠት ተጀምሯል።

የክትባቱ ማስጀመሪያ መርሃ- ግብር ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መለዕክት ያስተላለፉት የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታ ገርጊታ ክትባቱ ከዚህ ቀደመም እንደተሰጠ አንስተው ፣ ክትባቱ እስከምያልቅ ድረስ ትኩረት ሰጥተው እንደሚከታተሉ ገልጿል ::

የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳደሪና ውሃና ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኩሻቦ ኩሴ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ልጆቻቸውን ለዚህ ክትባት ማዘጋጀት እንደሚገባና በጥንቃቄ ያልወሰዱ ሁሉ እንድወስዱ ማድረግ እንደምገባ አጽኖት ሰጥተው ተናግሯል ::

ተግባሩን በይፋ ያበሰሩት የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ገላነህ ኩሴ እንደገለፁት በሽታዉን የማጥፋት ሥራ ከአለም አቀፍ ደረጃ ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃም ሰፊ ሥራ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

በዞኑ ከ65,575 በላይ ህፃናትን ለማስከተብ እየተሰራ ስለመሆኑ ያነሱት የመምሪያዉ ኃላፊ ለተፈፃሚነቱም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር በ5ቱም መዋቅር ላይ ያሉ ህፃናትን በመለየት እንዲከተቡ ሰፊ ሥራ ተሰርቶ ወደ ትግበራ መገባቱን አንስተዋል።

በመጨራሻም አቶ ገለነህ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበሽታውን አስከፍነት በመረዳት ህፃናት እንድከተቡ ማድረግ እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ::

ተገባሩ የማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ የዞኑ ጤና መምሪያው ኃላፊ ፣ የመምሪያው ምክትል ኃልፊ ፣የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳደሪና ውሃና ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊ ፣ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃልፊና የጤና ባለሙያዎች ተግኝተው ዘመቻውን በይፋ አስጀምረዋል ::

ከዚህም ባሻገር ህብረተሰቡ ለሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችለውን የመራጭነት ካርዳቸውን እንድወስዱ ጥሪ ቀርቧል ::

መጋቢት 21/2018 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *