ለአዲሱ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ አቀባበል እና ለቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ የሽኝት መርሃግብር ተካሂዷል

ለአዲሱ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ አቀባበል እና ለቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ የሽኝት መርሃግብር ተካሂዷል፣

ካራት:ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

የኮንሶ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ሠራተኞች ለአዲሱ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ አቀባበል እና ለቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ የሽኝት መርሃግብር አካሂደዋል፣

አዲሱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ በቢሮአቸው ከቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ጋር የስራ ርክክብም አድርገዋል።

ክቡር አቶ ገለቦ በስራ ርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት ህዝባችን አቅማችን ነው፤ህዝባችን ኃይላችን ነው! ያሉ ሲሆን አመራርነት እንደ ዱላ ቅብብሎሽ ነው፣ዛሬ ያለው ሰው የራሱን አሻራ ያሳርፋል ነገ ለሚመጣውም መልካም እና ተጨባጭ ውጤትን አስረክቦ ይሄዳል ብለው በቦታው የሚተካ ይበልጥ መትጋት እንደሚኖርበት አሳስበዋል።

አክለውም ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ ወደ ዞኑ አስተዳዳሪነት ሲመጡ ደስታዬ እጅግ የላቀ ነው፤አመራሮቻችን ዋናውን ትኩረት ለሠላም በመስጠት አስፈላጊውን ልማት መቀዳጀት ለመቀዳጀት በመደጋገፍ ለአርሶ አደሮቻችንና ለመላው ህዝባችን አይተከ ለሆነው ሠላም አጽንኦት መስጠት ይኖርበታል ብለዋል።

ህዝባችን ተለውጦ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንዲችል የተጀማመሩ መልካም መሠረቶችን ማስቀጠልና ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ተግባራትን አቀናጅቶ የሚጨበጡ ውጤቶችን ፣እንዲሁም አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል ።

ሠላም ከራስ ይጀምራል፤ ቅንነት አካባባቢን ወደ መልካምነት ይቀይራልና በሥልጣን ርክክቡ በጣም ደስተኛ ነኝ ብለዋል ሲሉም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጉራሾ ለሚታ በበኩላቸው ህዝባችን በርካታ የልማት ጥያቄዎችና ለየት ባለ መንገድ ደግሞ የመሠረተ ልማት ጥያቄ ያሉበት ህዝብ በመሆኑ አንዱ የሌላውን ድካም እያገዘ እጅ ለእጅ በመያያዝ የህዝባችን ጥያቄዎች ለመመለስ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የተጀማመሩ መልካም ተግባራትን ለማጠናከር እርስበርስ በደንብ መደጋገፍ ያስፈልጋል፤አመራሩ ቅንጅቱን በማጠናከር ለህዝባችን አስፈላጊውን ልማት መስራትም ይኖርብናል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ ህዝብን በቅንነት ማገልገል ለውጤት ያበቃል ያሉ ሲሆን ከቀድሞ ዋና አስተዳዳሪ ስራ ብቻ ሳይሆን ቅንነትና ትጋትን ተቀብያለሁ ብለው ባለንበት አንድነታችንና አብሮነታችንን ማጠናከር ይጠበቅብናል ሲሉ ገልጸዋል።

መሪ ይቀየራል ግን ሀገርና ህዝብ ይቀጥላል ስለዚህ ዋጋ በመክፈልና በትውልድ ላይ በመስራት ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም መታተር ከሁሉም ይጠበቃል በማለት ምክራቸውን ለግሰዋል።

የቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ አዲሱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳን ጨምሮ ለአዳስ የዞኑ ፊት አስተባባሪዎች የዋና አስተዳዳሪ ቢሮ እና በአዲስ መልክ የተሠራው ዘመናዊ የካቢኔ አዳራሽን አስጎብኝተዋል።

በመጨረሻም የቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ እና አዲሱ ዋና አስተዳዳሪ ለዶ/ር ኦንጋዬ ለተደረገላቸው አቀባበልና ሽኝት ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *