የዞኑ ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች ከፓስቃ-ፋሻ ከተማ እየተሠራ ያለውን መንገድ መስክ ምልከታ አደረጉ፣

በኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ የተመራው የዞኑ ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች ከፓስቃ-ፋሻ ከተማ እየተሠራ ያለውን መንገድ መስክ ምልከታ አደረጉ፣

‎ካራት:ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

‎በኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ የተመራው የዞኑ ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች የቀድሞው የዞን አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ በተገኙበት ከፓስቃ-ፋሻ ከተማ እየተሠራ ያለው መንገድ ስራን በመስክ ተመልክተዋል።

‎መንገዱ የወረዳው ዋና መንገድ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ጥገና ስላልተደረገለት የወረዳው ህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የቆየ ሲሆን አሁን የተጀመረው የመንገዱ ጥገና ስራ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ እየተሰጠ እንደመሆኑ መጠን ቅንጅታዊ አሠራር መጠናከር እንዳለበት ተገልጿል። የከና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ጋሊታ እንደገለፁት መንገዱ በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን የሚተዳደር መንገድ ሲሆን ለረጅም አመታት ጥገና ያልተደረገለት መንገድ በመሆኑ ከፍተኛ የእሮሮ ምንጭ ሆኖ የቆዬ ሲሆን ህዝብ ካለበት የመንገድ ችግር በጉልበት ጥገና እያደረገ መቆየቱን ገልፀው አሁን እየተደረገ ያለው የጥገና ስራን በሚፈለገው ለማጠናቀቅ የተጀመረው ቅንጅት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

‎የወረዳው ህዝብና መንግስት፣ የዞኑ ነጋዴ ማህበረሰብ እንዲሁም የዞኑ መንግስት በቅንጅት የመንገዱን ጥገና በፍጥነት ለመጨረሽ እየተረባረቡ መሆናቸውን ገልጸው በተለይ የነጋዴው ማህበረሰብ በስራው ያሳው እንቅስቃሴ እንድሁም የህዝብ ትብብርና ድጋፍ ለምርጥ ተሞክሮ ጭምር የሚቀርብ ነው ብለዋል።

‎‎የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ መንገድ የሁሉም አገልግሎቶች የደም ስር ሲሆን ያለ መንገድ መሠረተ ልማት ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የማይቻል መሆኑን አስገንዝበዋል።

‎ህብረተሰብን ማስተባበርና ለህዝብን ችግር ምላሽ ለመስጠት ዋጋ መክፈል እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ዶ/ር ኦንጋዬ፤አሁን የተጀመረው የነጋዴው ማህበረሰብ ድጋፍ፣የወረዳውና የዞኑ መንግስት ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም የወረዳው ህዝብ ተሳትፎ ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

‎የምልከታው ልዑክ የመንገድ ስራው በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለህዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

Konso Zone Government Communication.

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *