በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራው የቦርዱ፣ የዓለም አቀፍ አመራር አካላትና የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ያካተተ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገብቷል።

ልዑካኑ ኮንሶ ዞን ሲደርሱ፣ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ቡድን ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ስድስት የቦርድ ተወካዮችንና ከዙሪክ ዋና መሥሪያ ቤት የተወጣጡ ከፍተኛ የሥራ ባልደረቦችን ያካተተው ልዑክ ቡድኑ፣ ከአካባቢው ባህላዊ እሴቶች፣ ከማኅበረሰቡ የዕለት ተዕለት አኗኗርና ማኅበራዊ ሁኔታዎች ጋር ለመተዋወቅ የጋሞሌ አምባ መንደርን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱም ልዑካኑ የአካባቢውን ባህልና የማኅበረሰቡን አኗኗር በቅርበት እንዲያውቁ ዕድል ፈጥሯል።

በተጨማሪም በHEKS-EPER እና በኮንሶ ልማት ማኅበር ትብብር የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችን የመስክ ምልከታ ከማድረግ ባለፈ፣ በፕሮጀክቶቹ አፈጻጸምና በወደፊት የትብብር አቅጣጫዎች ዙሪያ ከኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪና ከልማት ማኅበሩ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    ለአዲሱ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ አቀባበል እና ለቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ የሽኝት መርሃግብር ተካሂዷል

    ለአዲሱ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ አቀባበል እና ለቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ የሽኝት መርሃግብር ተካሂዷል፣ ካራት:ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) የኮንሶ ዞን ከፍተኛ…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *