“ቃልን ባህል በማድረግ ብልጽግናችንን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው 9ኛው ዙር የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የአባላት ኮንፍረንስ ተጠናቀቀ፣

የመደመር መንገድን የመረጠ፣ እንደዚሁም ብልጽግናን ግብ አደርጎ የተጀመረ ፓርቲ አለን! – አቶ ሐመር ሐንሻ

“ቃልን ባህል በማድረግ ብልጽግናችንን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው 9ኛው ዙር የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የአባላት ኮንፍረንስ ተጠናቀቀ፣

በኮንፍረንሱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የዞኑ

ረዳት የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ የውብዳር ኦላታ በሀገር ግንባታ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ዘርፍ ሁሉም የህብረቱ አባላት ተባብረው በቅንጅት አብሮ መሠራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሐመር ሐንሻ በመክፈቻ ንግግራቸው የፓርቲያችን ጉዞ የመደመር መንገድን የመረጠ፣ እንደዚሁም ብልጽግናን ግብ አደርጎ የተጀመረ መሆኑን ጠቅሰው የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ሥራን ለማጠናከር ፣ ሁሉም አባል በቀጣይ ጊዜያት ከሚጠበቀው በላይ በመስራት ሁለተናዊ የሆነ ብልጽግን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ የራሱን አሻራ ማኖር አለበት ብለዋል።

የዞኑ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የ1ኛ ግማሽ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡትን አቶ መሃመድ ይመር በበኩላቸው ሁሉም የፓርቲ አባላት የራሳቸውን ዕድቅ በማቀድ ተግባራትን በአግባቡ እንዲፈጽሙና ጉደለት ይታይባቸው አፈጻጸሞች ቀጣይ ላይ እንዲሻሻሉ፣ በጥንካሬ የታዩት ደግሞ ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሁሉንም አባላት ርብርብ ይጠይቃል ሲሉ አስረድተዋል።

አቶ መሃመድ አክለውም አባሉ በሥነ ምግባር የታነፀ፣ ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን በመረጃ የሚታገል፣ መረጃን በሰለጠነ ቴክኖሎጂ የሚለዋወጥ መሆን አለበት አሉ ሲሆን፣ በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ያሉ መሻሻሎችን በማጠናከር አደረጃጀቶች ላይ እንደዚሁም አዳዲስ አባላት ማፍራት ላይ በብርቱ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የሥነ-ምግባር እና ኢንስፔክሽን ዕቅድ አፈጻጸምን ያቀረቡት አቶ ካፍታ ካስሞ በበኩላቸው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ተግባራዊ እንዲሆን ስራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ መስራት እንደሚገባ፣ እንደዚሁም ከዞን ማዕከል ጀምሮ እስከ ታችኛው መዋቅር ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ቀጣይ ላይ ከዚህ የበለጠ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የኮንፍረንሱ ተሳታፊ የብልጽግና ህብረት አባላት በአስተያየታቸው የፍትህ ተቋማት ገለልተኛና ነፃ መሆን እንዳለባቸው፣ የአካባቢያችን ሠላምና ደህንነት እንዲጠበቅ፣ ለሕብረተሰቡ የሚሰጡ የአገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ተግባራት በዕቅድ መሠረት እንዲሠሩ የጠቆሙ ሲሆን፣ እንደ ኮንሶ በጥንት አባቶቻችን ተጠብቆ ዛሬ ላይ የደረሰ ባህላችንን እና ቅርሶቻችንን በአግባቡ መንከባከብ እንደሚገባና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ይበልጥ ሊሰራበት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ተናግረዋል።

ኮንፈረንሱ ላይ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሐመር ሐንሻ፣ ረዳት የመንግስት ተጠሪና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ የውብዳር ኦላታ እና የህብረቱ አባላት ተገኝተዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

የካቲት 05/2017 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *