የተከበሩ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ አማካኝነት አቶ ገለቦ ጎልቶሞ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሆኑ በእጩነት ቀርበዋል።
የምክር-ቤቱ አባላትም የቀረቡትን እጩ አስመልክቶ አስተያየት ሰጥተው ሹመቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ገለቦ ጎልቶሞ በምክር-ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል፤ ከቀድሞው የዞኑ አስተዳዳሪ ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ ጋርም የሥራ ርክክብ አድርገዋል።
መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ









