ከታታሪዎች ምድር የተገኙ፣ በአፍላነታችው ጥበብ ያነፃቸው፣ በቁመናቸው ተፈጥሮ ያደላቸው፣ በብቃት ተፈትነው መከራን ተሻግረው ድልን የሰነቁ፣ ከራስ አልፈው ለሀገር የበቁ ጥበበኞች የተሰኙና ያልተነገረላቸው ብርቅዬ የኮንሶ ስፓርተኞች፥

በችሎታቸውና በልዩ የጫወታ ብቃታቸው ሁሌም ተመራጭ የሆኑ፣ ከሀገር ውስጥ ውድድር ጀምሮ እስከ ውጭ ሀገር የተመሙ፣ የወርቅ መዳሊያ እና ዋንጫ ሲሳያቸው ያደረጉ፣ የኢትዮጵያን ባንዲራ በአፍርካ አደባባይ ከፍ ያደረጉ ያልተዘመረላቸው ብቁ ስፖርተኞች፣
ኢትዮጵያን በዘርፉ ውጤታማ ያደረጉና ለራሳቸው የድል አክልል ከመድፋት አልፈው ለኢትዮጵያ ሴቶች ኩራት የሆኑ፥ በአትሌቲክስ፣ በውርወራ፣ በቦክስ እና በቮሊቦል ጫወታዎች በተለያዮ ክለቦች ውስጥ ያደጉና እያደጉ ያሉ ወጣቶችን ኮንሶ አፍርታለች።
በተለያዮ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት በፕሮጀክትና በክለብ ታቅፈው የራሳቸውን፣ የክለባቸውን፣ የቤተሰቦቻቸውንና የሀገራቸውን ስም የሚያስጠሩ ወጣቶችን የኮንሶ እናት አብራክ አፍርታ ለሀገር ፍሬ አብቅታለች።
ከበርካቶች የብሔራዊ የሴቶች የቮሊቦል ጥበበኞች ዛሬ በጥቂቱ ላጋተመራችሁ ወደድኩ
_________________

በኮንሶ ዞን ከኮልሜ ወረዳ የተገኙ ወጣት አዳነች አሰፋ እና ወጣት ታገሰች በኛ ይባላሉ፡፡ በአፍላ ዕድሜ ክልል ሳሉ ነበር ብሔራዊ የሴቶች መረብ ኳስ ክለብን የተቀላቀሉት፡፡
ወጣቶቹ በሔራዊ ቡድኑን ከተቀላቀሉ 3ኛ አመት አስቆጥረዋል፡፡ ሁለም ድል የሚቀናቸውና በጫወታቸው አሸናፊ የሆኑት ወጣቶቹ መዳሊያ፣ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት ተለይቷቸው አያውቁም፡፡
በ3 ዓመታቸው ውስጥ ዋንጫዎች ወርቅ መዳሊያዎች እና ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ያገኙት ዕንቁዎቹ የቮሊቦል ተጫዋቾች በሀገራቸው የውጤት ባለቤት ከመሆናቸው በላይ ኢትዮጵያን ወክለው በቱኒዚያ 2 ጊዜ እና በግብፅ ሀገር አንድ ጊዜ ብሔራዊ የሴቶች ቮሊቦል ውድድር ተጫውተው በማሸነፍ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ከፍ ያደረጉ ባለድል የኢትዮጵያ ሴቶች ክለብ ውስጥ ስሜ ገናናዎቹና ጥበኞች ናቸው ወጣት አዳነች አሰፋ እና ወጣት ታገሰች በኛ።
እነኛ ወጣቶች በአዲስ አበባ ብሔራዊ የሴቶች ቮሊቦል ተጫዋቾች ሲሆኑ በትምህርታቸው የተሳካላቸው፣ በስፖርቱ ውጤት የቀናቸው ከብርቅዬ የሀገራችን ስፖርተኞች ተርታ ተሰልፈዋል።
እኛም የህይወት ተሞክሮአቸውን ነገ ሰኔ 27/2016 ምሽት በሚኖረን የኮንሶ ዲጂታል ሬዲዮ ፕሮግራም በቀጥታ የሚሰራጭ ይሆናል ሠላም!
በቦክስና በሌሎች ልዩ ልዩ ስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ብርቅዬ ስፖርተኞቻችን በቀጣይ ክፍል እናስቃኛችኃለን።
መረጃው
ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሰኔ 26/2016












