ከ24 ሚሊዬን ብር በላይ የተገነቡ በሶላር ኃይል የሚሰሩ ውሃ ግንባታና እድሳት ፕሮጀክቶች ተጎበኙ።

MERCY CORPS ETHIOPIA የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በኮንሶ ዞን የሠራቸው በሶላር ኃይል የሚሠሩ የውሃ ተቋማትን ከክልልና ዞን የመንግስት አካላት ጋር የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

የኮንሶ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ መሣይ አሰፋ እንደገለፁት በዞኑ የውሃ ሽፋን ዝቅተኛ በመሆኑና ፕሮጀክቱ የሰራው ስራ መልካም መሆኑን አድንቀዋል።

ሜርሲ ኮርፕስን ጨምሮ ሌሎች ግብረሰናይ ድርጅቶች የውሃ ሽፋንን ከፍ ለማድረግ የበኩላቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ያሉት አቶ መሣይ፤ ህብረተሰቡ የሚሠሩ የውሃ ተቋማትን በባለቤትነት እንዲጠብቁና በጥንቃቄ እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

ምክትል አስተዳዳሪው አቶ መሳይ Mercy Corps ድርጅቱን በዞኑ መንግስትና ህዝብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጉዳይ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማሞ ሞሊሶ እንደተናገሩት ሜርሲ ኮር ድርጅት በዞኑ በውሃ ዘርፍ ያከናወናቸው ተግባራት የሚደነቁ ናቸው ብለዋል።

ድርጅቱ የእናቶችና የሴት ተማሪዎች እንግልትን ለመቀነስና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተሠራው የውሃ ተቋማትን እንደ አይን ብሌን መጠበቅ ይኖርበታል ብለዋል።

የዞኑ መንግስት ተግባሩን በቁርጠኝነት በመምራቱና በመከታተል ፕሮጀክቱን ውጤታማ ማድረግ ችሏል ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

በሜርሲ ኮር ኮንሶ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ በየነ ለማ በበኩላቸው ድርጅቱ በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የውሃ ችግርን ለመቅረፍ በፍትሃዊ ተደራሽነት ላይ እየሠሩ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በካራት ከተማ፣ ካራት ዙሪያ፣ ሰገን ዙሪያ፣ ከና እና በኮልሜ ወረዳዎች 34 የውሃ ቦኖዎች፣ አምስት የሶላር ኃይል እና ልዩ ልዩ የውሃ ሥራ ግንባታና እድሳት ተከናውነዋል ብለዋል።

ከ22 ሺህ ህዝብ በላይ ተጠቃሚ ያደረገው በሶላር ኃይል የሚሰራ ንፁህ መጠጥ ውሃ ሥራና ጥገና 24 ሚሊዬን 485 ሺ 258 ብር ወጪ በማድረግ በኮንሶ ዞን በተለያዩ አከባቢዎቸ‍እ የሚስተዋሉ የውሃ ችግሮችን ለማሻሻ ልማት ስራው ተከናውኗል።

የመስክ ምልከታው በካራት ዙሪያ ወረዳ ፉጩጫና ሶሮቦ ቀበሌያት እንዲሁም በካራት ከተማ አስተዳደር ዶካቱና ጋሞሌ ሰፈራት የተገጠሙና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የውሃ ቦኖዎች፣ ሶላርና መስመሮች የተመለከቱ ሲሆን ልዑካን ቡድኑ በምልከታው አበረታች ውጤት ማየቱን ገልጸዋል።

በመስክ ምልከታው የክልል፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የካራት ዙሪያ ወረዳ የስራ ኃላፊዎች ተግኝተዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

ግንቦት 25/2016 ዓ/ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *