ከበረሃማነት የፀዳ አካባቢን ለመፍጠር የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

“የመሬት ማገገም በረሃማነትና ድርቅን መቋቋም!” በሚል መሪህ የአካባቢ ጥበቃ ቀን በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ በችግኝ ተከላ መርሃግብር ተከብሯል።

የኮንሶ ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምንተስኖት ለሚታ በችግኝ ተከላ ወቅት እንደገለፁት የዓለም አካባቢ ጥበቃ ቀን በዓለም ለ51ኛ፣ በሀገራችንና ክልላችን ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ በዞናችን እየተከበረ መሆኑን ገልጸዋል።

በየዓመቱ ግንቦት 28 የዓለም አካባቢ ጥበቃ ቀን መሆኑን የተናገሩት አቶ ምንተስኖት፤ በአካባቢ ጥበቃ ቀን ዛፎችን በመትከል አካባቢያችንና ብዝሃ ህይወትን በመንከባከብ ጤንነታችንን መጠበቅ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የኮንሶ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ ቦጋሌ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም አካባቢያችን ለድርቅ ችግር የተጋለጠ በመሆኑ ይህ ክስተት እንዳይደግም ዛፍን ለመትከልና ለመንከባከብ ሁሉም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

አቶ ወንዱ ጨምረው የዓለም አካባቢ ጥበቃ ቀን ለዚህ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ያሉት ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ሁሉም የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት ላይ በንቃት እንዲሳተፍ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በኮንሶ ዞን የዓለም አካባቢ ጥበቃ ቀን በካራት ከተማ አስተዳደር የካራት ከተማ ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ የዞን፣ የካራት ከተማ አስተዳደር የፊት አስተባባሪዎች፣ የዞንና የካራት ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች በተገኙበት በችግኝ ተከላ ተከብሯል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

ግንቦት 29/2016 ዓ/ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *