በራሳችን አቅም የራሳችንን ችግር እንፍታ፤ሠላማችንን በጋራ እንጠበቅ

‎የኮንሶ፣ ኮሬና የጋርዱላ ዞኖች “በራሳችን አቅም የራሳችንን ችግር እንፍታ፤ሠላማችንን በጋራ እንጠበቅ”! በሚል መሪ ቃል የጋራ ሰላምን ለማጽናት የሶስትዮሽ የውይይት መድረክ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አካሂደዋል፣
‎
‎ካራት፣ ነሐሴ 2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)
‎
‎የሶስቱ ዞኖች የሰላምና ጸጥታ አካላት “በራሳችን አቅም የራሳችንን ችግር እንፍታ፤ሠላማችንን በጋራ እንጠበቅ”! በሚል መሪ ቃል በአካባቢው ያለውን ነባራዊ የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ በመገምገም በጋራ አሠራርና በመፍትሔ አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
‎
‎በውይይቱ የኮንሶ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ፎራ እንዲሁም ከኮሬና ጋርዱላ ዞኖች የተውጣጡ የሰላምና ጸጥታ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
‎
‎በመድረኩ በተለይም የሕግ በላይነትን ማስከበር፣ በሦስቱ ዞኖች መካከል የጋራ ሠላምን በማጠናከር፣የወየሳ ደንን መጠበቅ፣ የልማትና የሰላም ሥራዎችን በቅንጅት መከታተል እንዲሁም በአካባቢዎቹ የሚፈጠሩ ችግሮችን በጋራና በራስ አቅም መፍታት የሚቻልበት አቅጣጫ ተነስቷል።
‎
‎የኮንሶ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ፎራ፣ የጋራ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ቅንጅታዊ አሠራርን ከማጠናከር ባለፈ የሕግ በላይነትን በተግባር ለማረጋገጥ በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ገልጸዋል።
‎
‎ወንጀል ፈጽመው ከአንዱ አካባቢ ወደ ሌላ የሚሸሹ አካላትን በጋራ በመከታተልና ለሕግ አካላት በማቅረብ የሕግ በላይነትን ማስከበር እንደሚገባ የተጠቆመ ሲሆን ይህም በተቀናጀና ተከታታይነት ባለው መልኩ መፈጸም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
‎
‎አቶ ገዛኸኝ በተለይም የወየሳ ደንን ለመጠበቅ ቀደም ሲል በተደረገው የድንበር ማካለል ስራ መሠረት በመሥራት የጋራ ክትትልና ግምገማ ማካሄድ እንደሚገባ አሳስበው፣ የድጋፋዊ ክትትል ሥራዎችም በቼክሊስት በመደገፍ በሶስትዮሽ ቅንጅት እንዲከናወኑ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
‎
‎በመድረኩ በሦስቱ ዞኖች መካከል የጋራ ዕቅድና ማትሪክስ በማዘጋጀት የተጀመሩ ሥራዎችን በየጊዜው በጋራ በመገምገም፣ ከመሬት እውነታ ጋር የሚጣጣሙ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥና እስከታች ወርዶ መከታተል እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
‎
‎በተጨማሪም የወየሳ ደን ህልውናን መጠበቅ የሦስቱ ዞኖች የጋራ ኃላፊነትና የህልውና ጉዳይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ደኑ ለአካባቢው አርሶ አደሮችና ለማኅበረሰቡ ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ በጋራ ለመጠበቅ ቁርጠኛ አመራርና ተከታታይ ሥራ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።
‎
‎የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ የሕግ በላይነት በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባር መረጋገጥ እንዳለበት ገልጸው፣ በአካባቢዎቹ የሚፈጠሩ ችግሮችን በቅድሚያ በመለየትና በጋራ በመመካከር መፍታት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
‎
‎በተለይም ወንጀለኞችን ከንጹሃን ዜጎች በመለየት፣ ወንጀል የፈጸሙ አካላትን ለሕግ አካላት አጋልጦ በማቅረብና የሰላም አደናቃፊ ኃይሎችን በሕጋዊ መንገድ በመግታት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
‎
‎ተሳታፊዎቹ ካለፉ ችግሮች በመማር፣ለዘላቂ ሠላም ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችን ከላይ እስከታች ወርዶ መሥራት፣ሰላምና መግባባትን ማጠናከርና የሕግ በላይነትን በጋራ ማስከበር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
‎
‎በመጨረሻም የኮንሶ፣ ኮሬና ጋርዱላ ዞኖች የሰላምና ጸጥታ አካላት በጋራ ዕቅድ መሠረት ተከታታይ የክትትልና የግምገማ ሥራዎችን ለማከናወን፣ ግንዛቤ በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ተገቢውን ግንዛቤ ለመፍጠር፣ በጋራ የመፍትሔ አቅጣጫ ለመስጠትና በተቀናጀ አሠራር ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ከስምምነት ተደርሷል።

www.konsozone.org

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *