በካራት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በቅርቡ ለአገልግሎት የሚከፈቱ ፕሮጀክቶች ተጎበኙ

በካራት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በቅርቡ ለአገልግሎት የሚከፈቱ ፕሮጀክቶች ተጎበኙ

በኮንሶ ዞን ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመንግሥት፣ በሕዝብና በአጋር ድርጅቶች ትብብር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች ለምረቃናለአገልግሎት ማስጀመሪያ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ መሆኑ ተገለጸ።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የካራት ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ ፕሮፌሰር ዲላዮ በቀለ የተመራው ልዑክ፣ በሆስፒታሉ እየተገነባ ያለውን ምቹ ክሊኒክ ግንባታን የጥገና ስራን ጨምሮ በርካታ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክቷል።

በምልከታው የፕሮጀክቱ ኢንጅነሪንግ ቡድን የክሊኒኩን የክፍሎች አደረጃጀት፣ ተደራሽነትና ለተጠቃሚዎች ምቹነት በመመልከት በቀሪ ሥራዎች ላይ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦች በመስጠት ፣ በተለይም የመብራትና የውሃ አቅርቦት በተሟላና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ እንዲጠናከር አፅንዖት ተሰጥቷል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ግርማ በሌ፣ የሆስፒታሉ ፕሮጀክት ቀደም ሲል የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸው፣ በተለይ ምቹ ክሊኒክ መገንባቱ የሚያስመሰግን ሥራ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ግርማ አክለውም፣ የዞኑ መንግሥት ፕሮጀክቱ በጥራትና በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅና ለሕዝቡ ሙሉ አገልግሎት እንዲጀምር ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የካራት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኩሴ አድማሱ በበኩላቸው፣ በሆስፒታሉ እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶች በዞኑ መንግሥት ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቁመው፣ ሥራዎቹ በተያዘላቸው ጊዜና በሚፈለገው ጥራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የካራት ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ ፕሮፌሰር ዲላዮ በቀለ በበኩላቸው፣ በካራት ከተማ የተጀመረው የምቹ ክሊኒክ ግንባታ ከጤና ተቋሙ ጋር በተያያዘ የሚደረገው ድጋፍ አካል መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ አንጻር በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ለውጥ መታየቱን ገልጸው ፣ ቀሪ ክፍተቶችንም በተቻለ አቅም ለመሙላት ድጋፉ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም ቀሪ ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ በማጠናቀቅ በካራት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በቅርቡ ለሕዝቡ አገልግሎት እንዲከፈቱ ለማድረግ የዞኑ መንግሥት፣ ሆስፒታሉና አጋር አካላት በትብብር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *