የኮንሶ ዞን ብልፅግና ኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን የ2018 ዓ.ም የ2ኛ መንፈቀ ዓመት የአመራር ግምገማና ምዘና አካሄደ





ካራት፦ ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን )
የኮንሶ ዞን ብልፅግና ኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ መንፈቀ ዓመት የኮሚሽኑ አመራር ግምገማና ምዘና መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የክልሉ ኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴ አባልና የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደለለኝ ብሩ ተገኝተዋል።
አቶ ደለለኝ ብሩ እንደገለጹት፣ የኮሚሽኑ አመራሮች በበጀት ዓመቱ ለተሰጣቸው ተልዕኮ ትኩረት በመስጠት በሀገራዊ፣ በክልላዊና በዞናዊ ተልዕኮዎች ላይ በትኩረት ሰርተዋል።
የግምገማና ምዘና መድረኩም በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል፣ በጉድለት የተለዩ ጉዳዮችን በመለየትና ለእነዚህም የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ለቀጣይ ተልዕኮ የተሻለ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችል መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
አያይዘውም ኮሚሽኑ የፓርቲውን የፖለቲካ ጤና በመጠበቅ፣ የአባላትን መብት በማስከበርና የፓርቲውን ሀብት በመጠበቅ የሚጫወተው ተቋማዊ ሚና እንዳለ ጠቁመው፣ ኮሚሽኑ ተልዕኮውን በተጠያቂነትና በተቋማዊ አቅም ማጠናከር እንደሚገባው አሳስበዋል።
በመድረኩ የዞኑ ምክር ቤት የመንግሥት ሀብት ቁጥጥርና የበጀት ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የኮሚሽኑ ሰብሳቢ አቶ አያኖ ካውዳይታን ጨምሮ የኮሚሽኑ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም በግምገማው የተለዩ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል፣ የታዩ ክፍተቶችን ማረምና የኮሚሽኑን ተቋማዊ አቅም በማጠናከር በቀጣይ የተሰጠውን ተልዕኮ በተሻለ ውጤት ለመፈፀም በጋራ መሥራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
www.konsozone.org






