የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጅነሪንግ ቡድን የኮንሶን ባህላዊ ቅርስ የሆነውን የጋሞሌ አምባ መንደርን ጎበኙ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጅነሪንግ ቡድን የኮንሶን ባህላዊ ቅርስ የሆነውን የጋሞሌ አምባ መንደርን ጎበኙ

ካራት፤ ነሐሴ 06/2018 ዓ/ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን )

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጅነሪንግ ክፍል የተውጣጣ የኃላፊዎችና የባለሙያዎች ቡድን በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስ/ር ከሚገኙ አምባ መንደራት መካከል ጋሞሌ አምባ መንደርን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ወቅት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ግርማ በሌ ለቡድኑ ስለ ጋሞሌ አምባ መንደር፣ ስለአካባቢው ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶች እንዲሁም ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ ስለመጡ የኮንሶ ህዝብ ሀገር በቀል እውቀትና ጥበብ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በአካባቢው ከሚገኙ ታሪካዊ ሥራዎችና ቅርሶች መካከል የካብ፣ ህዝቡ የሚወያይባቸውና የሚማከርባቸው እንዲሁም ባህላዊ እርቅ ስነ ስርዓት የሚከናወንባቸው ሞራዎች፣ የትውልድ ማሸጋገሪያ ኦላሂታና ትክል ድንጋዮች ብሎም ሌሎች በጥንት ዘመናት የተሰሩ የኮንሶ ህዝብ ባህላዊ ዕሴቶችን አስተዋውቀዋል።

በተጨማሪም በኮንሶ ባህላዊ ሥርዓት ዳኝነትና ማህበራዊ ጉዳዮች የሚፈቱባቸው ባህላዊ ሥርዓቶች፣ በዳይና ተበዳይ የሚለዩባቸው ባህላዊ ስርዓቶች፣ የተደበቁ ጥፋቶችን በባህላዊ መሃላ መንገድ ለመፍታት የሚያግዙ ሥርዓቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።

የአካባቢው አወቃቀር፣ ከአጎራባች ዞኖች ጋር ያለውን ቁርጠኝነት ፣ የጥንቱ የንግድ ሥርዓት፣ ከከፍተኛ ደረጃ እስከ ዕለታዊ ኑሮ የሚመሩ ሕጎችና ደንቦች እንዲሁም እነዚህ ሥርዓቶች በትውልድ መካከል ተጠብቀው መቆየታቸው ለቡድኑ በሰፊው ተብራርቷል።

የካራት ከተማ ከንቲባ አቶ ጋሻሁን ኩሲያ በበኩላቸው፣ ቡድኑ በጉብኝቱ ያየው የኮንሶ ህዝብ ታሪካዊና ባህላዊ እሴት አስደሳች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከዘመናት በፊት የተመሰረቱ ባህላዊ ሥርዓቶችና አወቃቀሮች እስከዛሬ በአካባቢው ተጠብቀው መቆየታቸውን በማድነቅ፣ የኮንሶ ህዝብ ባህላዊ እውቀትና የራሱን ማህበራዊ ሕይወት በራሱ ሥርዓት የማደራጀት ችሎታ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።

ከከንቲባው አባባል መነሻነት፣ ይህ ዓይነቱ ጉብኝት ከባህላዊ ቅርሶች ከማየት ባለፈ የኮንሶ ህዝብን ታሪክ፣ ሀገር በቀል ዕውቀትና የአኗኗር ዘይቤ በቀጥታ ለመረዳት ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎችና አመራሮች የጋሞሌ አምባ መንደር መጎብኘታቸው፣ በኮንሶ ዞን ለሚከናወነው የሳብስቴሽን ፕሮጀክት ከሚያከናውኑት ቴክኒክ ምልከታ ጎን ለጎን የአካባቢውን ታሪክና ባህል እንዲያውቁ ዕድል ፈጥሮልናል ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ብበጊጊያ ግና

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *