የኮንሶ ምርጫ ክልል ጽ/ቤት ጊዜያዊ የምርጫ ውጤትን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮንሶ ምርጫ ክልል ጽ/ቤት ጊዜያዊ የምርጫ ውጤትን ይፋ አደረገ

ግንቦት 30/2018 ዓ.ም. ( ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮንሶ ምርጫ ክልል ጽ/ቤት በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ምርጫ ክልል ለተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት የተካሄደውን ምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ አድርጓል።

ጽ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ በኮንሶ ምርጫ ክልል በተካሄደው ምርጫ የተመዘገቡ መራጮች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በሰላማዊና ሥርዓታማ ሁኔታ በመጠቀም በምርጫው በንቃት ተሳትፈዋል።

በዚህም መሠረት ለተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት የተሰጡ ድምጾች ቆጠራ ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ መደረጉን ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

የምርጫ ቦርዱ የኮንሶ ምርጫ ክልል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሽ ግሐኖ እንደገለጹት፣ ይህ ውጤት ጊዜያዊ በመሆኑ ማህበረሰቡ የምርጫ ቦርዱን ይፋዊ መረጃዎች ብቻ እንዲከታተል እና በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን እንዳይቀበል ጥሪ አቀርበዋል።

የኮንሶ ምርጫ ክልል ጽ/ቤት ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ እንዲካሄድ ላደረጉት አስተዋጽኦ ለመራጩ ሕዝብ፣ ለተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለጸጥታ አካላት፣ ለኮንሶ መብራት ኃይል፣ ለምርጫ አስፈጻሚዎች እና ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።

በጊያ ግና

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *