ክህሎትን መሠረት ያደረገ የስራ ዕድልን በመፍጠርና የንግዱ ዘርፍ ማዘመን እንደሚገባ ተጠቆመ።

በኮንሶ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ዞናዊ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ፣ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ በመቀናጀት የኑሮ ውድነትን ማረጋጋትና ስልጡን ትውልድ ማፍራት እንደሚገባም አስታውቀዋል።

_____________

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ አያኖ ካውዳይታ እንደገለፁት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ክህሎትን መሠረት ባደረጉ ስልጠናዎች የስራ ዕድል መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ንግድና ገበያ፣ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ቴክኒክና ሙያ ሴክተሮች በቅንጅት ክህሎትን መሠረት ባደረጉ ስልጠናዎች በትኩረት በመስራት አካባቢን ብሎም ሀገርን መቀየር እንደሚቻል ልዩ አማካሪው አቶ አያኖ አስገንዝበዋል።

የኮንሶ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ኩሲያ ለዜጎች በክህሎት የዳበረ ስራ ዕድልን በመፍጠር የንግዱ ዘርፉን በማዘመን፣ የውጭ ንግድ ምርት ግኝት ማሳደግና የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኮንሶ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሣሁን ገረመው በሀገራችን ብሎም በዞናችን በየጊዜው በተለያዩ ምክንያቶች እየጨመረ የመጣው የስራ አጥነት ችግር በአሁኑ ጊዜ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተግዳሮት ሆኖ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ለሀገር ዕድገትና ልማት መፋጠን እንዲሁም ሠላምን ማረጋገጥ ለስራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ አስፈላጊ መሆኑንም የመምሪያው ኃላፊ አቶ ካሣሁን በልዩ ትኩረት በንቅናቄ የሚሠሩ ስራዎች ዕቅድ ሰነድ በሚያቀርቡበት ወቅት ገልጸዋል።

የኮንሶ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ገብረሃና ገቢኖ በበኩላቸው ክህሎትን መሠረት ያደረገ የስራ ዕድል ፈጠራ በለሌበት ውጤታማ መሆን አይቻልም ብለዋል።

በዘርፉ ውጤታማ ለመሆን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ሴክተር በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የኮንሶ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪና የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ ቦጋሌ በበኩላቸው የኑሮ ውድነትን ማረጋጋትና ክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ የ100 ቀናት ዕቅድ በመሆናቸው በንቅናቄ በመስራት፣ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

አቶ ወንዱ ጨምረው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋትና ክህሎት መር ስራ ዕድል ለመፍጠር በብድር አመላለስ እንዲሁም የሰንበት ገበያዎችን በየመዋቅሮች የማስፋፋት ተግባር ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ጉዳይ መሆኑንም አሳስበው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ አያኖ ካውዳይታ ስራ አጥ ወጣቶች ስራን ሳያማርጡ በክህሎት መር ስራ ዕድል እንዲሰማሩ ለማድረግ የታችኛው መዋቅሮች በተቀመጠው የማስፈፀሚያ ስልት መሠረት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩ ከዞን ማዕከል ጨምሮ የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የፊት አመራሮች፣ የዘርፉ ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ ነጋዴ ምክር ቤትና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *