አንድ ሀይማኖት የሰላም አሴት ግንባታን መቻቻልን፣ አብሮነትን፣ ፍቅርን፣ ይቅርታን እና አንድነትን መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ

አንድ ሀይማኖት የሰላም አሴት ግንባታን መቻቻልን፣ አብሮነትን፣ ፍቅርን፣ ይቅርታን እና አንድነትን መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኮንሶ ዞን አስተዳደር ጽፈት ቤት ጋር በመተባበር የኮንሶ ዞን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መስረታ አካሂደዋል።


መድረኩ በጸሎት የተጀመረ ሲሆን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የኮንሶ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ጉራሾ ለሚታ ሰላምን በማስከበር ሂደት የሀይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፥ ለአንድ ማህበረሰብ እድገት ሀይማኖት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪና የእለቱ ክብር እንግዳ አቶ አያኖ ካውዳይታ በበኩላተቸው ፎረሙ በመመስረቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ሰላምን በማስፈን ሂደት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሀይማኖት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልፀዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ መላከሰላም ኦኪቻ እንጋ የሀይማኖት አባቶች የሰላም መልእክተኞች ነን ብለው ሰላም በሌለበት ሀይማኖታዊ ስርአቶችን መፈጸም አይቻልም ብለው፥ አምላካችን የሰጠንን ሰላም መጠበቅ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የሰላም ግንባታና የብዝሀነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ በቀለ ሎኮርማ በበኩላቸው ስለ ሰላም መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለሰላም አሴት ግንባታ መቻቻል፣ አብሮኘት፣ ፍቅር፣ ይቅርታ እና አንድነትን መከተል እንደሚገባ በዝርዝር አብራርተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ መጋቢ ጊዮርጊስ ጎአ የሀይማኖት ተቋማት አመሰራረትና አሰራር በሚል ርእሰ ጉዳይ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት በሰላም በፍቅር፣ በመቻቻል ለጋራ ጥቅም መስራት ይገባናል ብለዋል።

የሀይማኖት ጉባኤ እኩልነት የሰፈነበት ኢትዮጵያን ማየትን አላማው አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸው ጉባኤው በሰባቱ የሀይማኖት ተቋማት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ፣ በእስልምና፣ የካቶሊክ፣ በቃለህይወት፣ በመካነ ኢየሱስ፣ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት እና በወንጌላዊያን ቤተ እምነቶች የሚቋቋም ጉባኤ መሆኑን ገልጸዋል።

ህጋዊ ያልሆኑ ተቋማትን፣ አግባብ ያልሆነ የድምጽ ብክለት እና ያልተካተቱ የሀይማኖት ተቋማትን በተመለከተ ህጎች እየተዘጋጁ መሆናቸውን እና ሲደርሱ ይፋ እንደሚደረጉ ከመድረኩ ተገልጿል።

በመጨረሻም የየሀይማኖቱ ተወካዮች ከክልሉ የሀይማኖት ጉባኤ የምስረታ ሰነድ ተቀብለዋል።

መረጃው
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ
ግንቦት 08/2016 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *