
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ገልገሎ ገልሾ ለህዝቤ ሙስልሙ ማፍጠሪያ የሚሆን ተምር አበረከቱ፡፡
Copyright ©konso Zone gov’t communication dpt
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ገልገሎ ገልሾ ለህዝቤ ሙስልሙ ማፍጠሪያ የሚሆን ተምር አበረከቱ፡፡
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ እና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻካይቶ ሳይሙሮ በፆም ላይ ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድምና እህት ማህበረሰብ ለማፍጠሪያ የሚሆን ተምር አበረከቱ፡፡
ረመዳን ፆም ህዝቤ ሙስልሙ ስለ ሀገር ሠላም የሚያስብበት፣ ስለ ፍቅር የሚኖርበት ውድ ወር በመሆኑ ፆሙን በሠላም እንዲያሳልፉ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪና ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ በጋራ ተመኝተዋል፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ ስጦታውን ባበረከቱበት ወቅት እንደተናገሩት የእስልምና እምነት ተከታዮቻችን በዚህ ወቅት ስለ ሀገርና ህዝብ ሠላምን የሚያስቡበትና ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙበት ወቅት በመሆኑ ፈጣሪ ብርታቱን እንዲሰጣቸውም ተመኝተዋል፡፡
ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ያገኙትን ስጦታ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳደሩ አቶ ገልገሎ፤ ለህዝቤ ሙስልሙ ሲያበረክቱ ማፍጠሪያው ብታንስም በአብሮነት መቋደስ ልምዱ የሆነው የሙስልሙ ማህበረሰብ፥ የተደረገችውን የተምር ስጦታ በፍቅር እንዲቋደሷት በፍቅር አበርክተዋል፡፡
በኮንሶ ዞን የኃይማኖት ፎረም ምክትል ሰብሳቢና የእስልምና እምነት ጉዳይ ጽ/ቤት ሰብሳቢ ሙስጠፋ አያኖ ስጦታውን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ይህ ስጦታ ከዚህ ቀደም ያልተለመደና ያልተጠበቀ ታላቅ ስጦታ በመሆኑ በመስጂዱ ስም ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል፡፡
ከዞኑ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት ለተደረገልን ስጦታ ታላቅ አክብሮት አለን ያሉት እስልምና ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ሙስጠፋ፤ በዚህ የጾም ወቅት አስባችሁ ላደረጋችሁልን ማፍጠሪያ በህዝቤ ሙስልሙ ስም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም አሉ ሙስጠፋ፤ በዚህ ፆም ወቅት በየትኛውም እምነት ውስጥ ያላችሁ ወጣቶች ራሳቸውን በመግዛት፣ በበይነ መረብ ጥላቻን ከመዝራት እንዲቆጠቡ እና ጊዜውንና ዕውቀቱን ለመልካም ነገር ብቻ በማዋል ውድ የሆነውን የረመዳን ወርን በፍቅር፣ በሠላም፣ በመከባበር፣ በመደጋገፍና ከፈጣሪ በረከትን ለማግኘት እንዲተጉ መክረዋል፡፡
መረጃ
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
መጋቢት 26/2016 ዓ.ም








