የተደራጀ የሴቶች ሚዲያ ሰራዊት በመገንባትና የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀም ስርአትን ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቆመ።

የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ እና ሣይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ በጋራ በመተባበር “ሴቶችና ቴክኖሎጂ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪህ ቃል ለተለዩ የሚዲያ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

_____________

የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሳምራዊት አዳኔ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው እንደገለፁት የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተግባር በጋራ ተግባቦትን መፍጠር ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሠራዊት ዲባባ በበኩላቸው በስልጠናው ይዘት ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

ዓለማችን በቴክኖሎጂ ዘመን ሴቶችን በዲጂታል ሚዲያ የአጠቃቀም ስርአት ማጎልበትና ማብቃት፣ ሀሰተኛና የጥላቻ ንግግሮችን በንቁ የሴቶች አደረጃጀት ማምከን፣ ለገጽታ ግንባታ ብቁ የሆኑ ሴቶች ማፍራት አስፈላጊ መሆኑን አቶ ሠራዊት ዲባባ ጠቁመዋል።

የስልጠና አጠቃላይ ይዘት በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩር መሆኑን የገለፁት አቶ ሠራዊት፤ ስኬታማ ተግባቦት፣ የመረጃ ስርጭት ክህሎት፣ አፍራሽ አጀንዳዎችን ሀሰተኛና የጥላቻ ንግግሮችን ማምከን እንዲሁም በሚዲያ አጠቃቀም ክትትል ግምገማና ትንተና ርዕሰ ጉዳዮች የሚዳስስ መሆኑን አብራርተዋል።

የኮንሶ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንዱ ቦጋሌ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ሴቶች የማህበረሰቡ አንድ አካል በመሆናቸው አሁን ባለንበት ወቅት ሴቶችን በቴክኖሎጂ ማብቃት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሴቶች ማብቃት ማህበረሰብን ማብቃት ነው! ያሉት ረዳት የመንግስት ተጠሪው አቶ ወንዱ፤ ሴቶች በተፈጥሮ በዓላማ ጽኑ በመሆናቸው ሀሰተኛ የጥላቻ ንግግሮችን በትክክለኛ መረጃ ስርጭት ማምከን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የቴክኖሎጂ ተግባቦትን በመፍጠር የዲጅታላይዘሽን መሰናክሎችን በመጣስ ብቁ የሆኑና በቴክኖሎጂ የዳበሩ ሴቶች ማፍራት ያስፈልጋልም ብለዋል።

የሴቶች ስነ ልቦና መገንባት፣ ሴቶች በሚዲያ ዘርፍ የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠርና በራሳቸው የሚተማመኑ ንቁና ብቁ ሴቶች ማፍራት የስልጠናው ዓላማ መሆኑን በኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የማህበራዊ ሚዲያ አዘጋጅ ባለሙያ ወ/ሪት ኤደን እስጢፋኖስ ሰነዱን ባቀረበችበት ወቅት ተናግራለች።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሁለገብ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ባለሙያ አቶ ጊያ ግና በዲጂታል ሚዲያ ፕሌትፎርሞች አጠቃቀም፣ አዘገጃጀትና ደህንነት ጥበቃ ዙሪያ ተግባር ተኮር ግንዛቤ አስጨብጠዋል።

በቀረቡ ሰነዶች ዙሪያ ሀሳብና አስተያየታቸውን የሰጡ ተሳታፊዎች እንደገለፁት በዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን እና ሣይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ የተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከግንዛቤ ባሻገር የስነ ልቦና ግንባታ ስልጠና መሆኑን ገልፀው ሞራላዊ ንቃት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።

ስልጠናው የፈጠረብን መነቃቃት ከአሰልጣኞቹ መረዳት ችለናል ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ ስልጠናው በውስጣችን የነበረ ፍርሃትን የሚያስወግድ በመሆኑ አቅራቢዎችን አመስግነዋል።

ሃሳብን በነፃነት መግለጽ፣ ንቁ የሚዲያ ሰራዊት መሆን የሚያስችለን፣ የኮሚኒኬሽን ተግባር አጋዥ ግንዛቤ በመሆኑ የስልጠና ሰነዱን ያሰናዳው የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያን አድንቀዋል።

እንደ ሰልጣኞቹ ገለፃ የሰለጠንነው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በፖለቲካዊ እይታን ለታችኛው የህብረተሰባችን ክፍል ለሚገኙ ሴቶች እህቶቻችን በማጋራት ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሳምራዊት አዳኔ በማጠቃለያቸው በሚዲያ አጠቃቀማችን እንደ ግለሰብ ሳይሆን እንደ ሀገር ያሉንን አደረጃጀቶቻችንን በቅንጅት በማጠናከር ይገባል ሲሉ መክረዋል።

በቅንጀ‍እትና በትብብር ስልጠናውን ያዘጋጁት የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እና ሣይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያዎችን በፓርቲው ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም የዞኑ ሴቶች ሊግ የመሠረታዊ ድርጅት አመራሮች፣ የህዋስ አደረጃጀቶች እና የሚዲያ ሰራዊት መሪዎችን በመሰየም ተሳታፊዎች በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

                  መጋቢት 27/2016 ዓ/ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *