በኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ የሚገኘው የማሶያ ቀበሌ የሶላር ፕሮጀክት ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ የፌዴራል ፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ጎበኙ

በኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ የሚገኘው የማሶያ ቀበሌ የሶላር ፕሮጀክት ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ የፌዴራል ፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ጎበኙ

የኢፌዴሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታና የኮንሶ ምርጫ ክልል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ የኮንሶ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የኮንሶ ምርጫ ክልል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እጩ ወ/ሪት አዳነች ኩሼታ፣ የኮንሶ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጉራሾ ጎስከ እንዲሁም የዞኑና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ ማሶያ ቀበሌ ተገኝተው በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የሶላር ኃይል ፕሮጀክት ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል።

አመራሮቹ በጉብኝታቸው ወቅት በቀበሌው እየተገነባ ያለው የሶላር ፕሮጀክት ለህብረተሰቡ የመብራት አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ በአካባቢው የልማት እንቅስቃሴን እንደሚያፋጥን ገልፀዋል።

በጉብኝቱ ላይ የወረዳው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከመብራት ኃይል ሪጅኖች የመጡ ባለሙያዎችና የቀበሌው አመራሮች በመሳተፍ የፕሮጀክቱን የአፈፃፀም ደረጃ ገምግመዋል።

በውይይቱም ቀሪ የመብራት ዝርጋታ ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ህብረተሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ሁሉም አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።

አመራሮቹ የብልጽግና ፓርቲ የልማት እሳቤ መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት የህዝብን ኑሮ ማሻሻልና የገጠር አካባቢዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑን በመግለፅ የፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *