”ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ!” በሚል መሪህ ቃል የደቡብ ኢትዮጽያ ክልላዊ መንግስት ደንና አከባቢ ጥበቃ ልማት ቦሮ ክልል አቀፍ የብክለት መከላከል ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው።

”ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ!” በሚል መሪህ ቃል የደቡብ ኢትዮጽያ ክልላዊ መንግስት ደንና አከባቢ ጥበቃ ልማት ቦሮ ክልል አቀፍ የብክለት መከላከል ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው።

የፕላስቲክ ብክለት በሰውና በእንስሳት ጤና ላይ ከፍተኛ ችግር እያደረሰ እንደሚገኝ የኢፌዴሪ አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ የአከባቢ ብክለት በከፍተኛ ደረጃ የጤና ችግር የሚያስከትል ሲሆን ጥናቶች እንደሚጠቆሙት በ2015 በጥቅሉ 4.6 ትርልዮን ዶላር የሚጠጋ የአኢኮኖሚ ጉዳት አደርሷል ብለው።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ፥ በበለፀጉ ሀገራት የሚከሰተዉ ብክለት ጉዳቱ በታዳጊ ሀገራት ላይ ይበረታል ብለዋል።

አከባቢን መጠበቅ የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ የክልሉ ምክር ቤትም ብክለትን ለመከላከል የተለያዩ አዋጆችን ማጸጽደቁን ጠቁመዋል።

የክልሉ ዋና አፌ ጉባአኤዋ ለቀጣዮቹ 6 ወራት በሚቆየዉ የብክለት መከላከል ዘመቻ ሁሉም በክልሉ ያሉ ተቋማትና ህብረተሰብ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቴ ግጄ አካባቢን መጠበቅ፣ የሰውን ጤንነትና የተፈጥሮን ሥነ ውበት ማቆየት የሁሉም ዜጋ ተግባርና ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

እንደ ኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት ጥናት በአለም አቀፍ ደረጃ የአየር ብክለትን ዘጠኝ ሚሊዮን ያለ ጊዜው ሞት እና 2.6 ትሪሊዮን ዶላር ለህመም ህክምና ወጪ አስከትሏል ብለዋል አቶ ግዛቴ ግጄ።

በንቅናቄ መድረክ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ፣ የኢፌዴሪ አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየው ባዉዲ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቴ ግጄ፣ የሁሉም ዞኖች ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የሁሉም ዞኖች ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሚያዚያ 10/2016
አርባምንጭ

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *