በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ተነሳሽነት የተጀመረው አንድ ተራራን የማልማት ንቅናቄ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች ከተመረጡ 10 ዞኖች አንዱ ኮንሶ ሲሆን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ሰነዱን ተቀብለዋል።
ዞናዊ ስትራቴጂክ ሰነዱ በኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ጎጫ ቀበሌ የተጀመረውን አንድ ተራራ የማልማት ዘመቻ ተግባራዊ ለማድረግም ተፈራርመዋል።
እንሰራለን! እናለማለን! የለማችና የበለፀገች ምቹ ኮንሶን ለትውልድ እናወርሳለን! የኮንሶን ታታሪነት ዳግም ከፍ እናደርጋለን! ሲሉም ዋና አስተዳደሩ ተናግረዋል።
መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሚያዚያ 10/2016
አርባምንጭ







