“ፅዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪህ ቃል የፅዳትና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
የንቅናቄ መድረኩ በአባቶች ቡራኬ የተጀመረ ሲሆን ሁሉም ሠላሙን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ለአካባቢው ጽዳት ትኩረት መስጠት ይኖርበታል ብለዋል።
የካራት ከተማ ከንቲባ አቶ ፍሬዘር ኮርባይዶ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው እንደተናገሩት በከተማ ፅዳት፣ ውበት እንዲሁም በግልና በአካባቢ ንፅህና ዙሪያ ሁሉም ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል ብለዋል።
ከንቲባው አክለው በከተማችን በተለያዩ አካባቢዎች ቆሻሻዎችን ያለ አግባብ ጥንቃቄ በጎደለው መንገድ የሚያስወግዱና የከተማን ፅዳት የሚያበላሹ አካላት መኖራቸውን ገልፀው እነዚህ አካላት ከድርጊቱ ሊቆጥቡ ይገባል ብለዋል።

የኮንሶ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሣይ አሰፋ በበኩላቸው ፅዱ፣ ውብና አረንጓዴ ከተማ ለብልጽግና ጉዞ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ በመሆናቸው ትኩረት ሰጥተን የከተማችን ሁለንተናዊ ፅዳት መጠበቅ ይኖርብናል ብለዋል።
የኮንሶ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሳይ አሰፋ በበኩላቸው በከተሞች ህዝብ ተጠጋግቶ የሚኖርበት አከባቢ በመሆኑ የከተማ ፅዳት የተጠበቀ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
አቶ መሣይ፤ የምርቶች ተረፈ ምርትና ቆሻሻዎችን በአግባቡ በማስወገድ ከማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ችግር ራሳችንን ሊንጠብቅ ይገባል ብለዋል።

ከተሞች ፅዱና ውብ ካልሆኑ አየር ንብረት ብክለትን በማስከተል ህዝባችንን ሲለምጎዳ በፅዳት፣ ውበትና በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ህዝባዊ ተሳትፎ ወሳኝነት እንዳለው አቶ መሣይ ጠቁመዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ቢሮ ኃላፊና የእለቱ ክብር እንግዳ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ እንደተናገሩት ካራት ከተማ የዓለም ቅርስ መገኛ ከመሆኑም ባሻገር የተለያዩ ቱሪስቶች የሚመላለሱባት፣ የክልሉ አንድ ማዕከል፣ የዞኑ መቀመጫ፣ የካራት ዙሪያ ወረዳ ማዕከል ብሎም በዩኔስኮ የተመዘገቡ አምባ መንደራት መገኛ በመሆኗ ለእነዚህ ሁሉ የሚመጥን ከተማ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ፅዳት ለራስ፣ ለህዝብ፣ ለአካባቢ ብሎም ለሀገር አስፈላጊ በመሆኑ ጤንነቱ የተጠበቀ ዜጋን ለመፍጠርና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ፅዳትን የዘወትር ልማዳችን ሊናደርግ ይገባል ብለዋል።
አስተያየት ሰጪ ተሳታፊዎች እንዳሉት ንፅህና ከራስ ይጀምራል ሲቀጥል ወደ አካባቢ ስለሚሄድ ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ እንዲሁም ቆሻሻን ያለአግባብ የሚያስወግዱ አካላትን ለህግ በመጠቆም በአንድነት ለአካባቢያችን ንፅህና ዘብ መቆም ይጠበቅብናል ስሉ ተናግረዋል።

ከተማችን የዞኑ፣ የክልሉ ብሎም የዓለም አቀፍ ቅርስ መገኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከተማችንን ፅዱና ምቹ ለማድረግ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች መረባረብ ይኖርብናል ሲሉ በአስተያየታቸው ተደምጠዋል።
የግል ንፅህናን ከመጠበቅ ባሻገር የአካባቢ ንፅህና ገጽታን የሚያበላሹና ቆሻሻን በየቦታው የሚጥሉትን ለመቆጣጠር ህዝቡ በራሱ ተደራጅቶ አካባቢውን ከብክለት መከላከል አለበት ብለዋል።

በመጨረሻም ተሳታፊዎች የከተማ ፅዳትና የችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሂደዋል።







