የኮንሶ ዞን ሠራተኞች ሠራተኞችና አመራሮች የጋራ የአቋም መግለጫ
የኮንሶ ህዝብ በስራ ታታሪነቱ በዓለም ያስመሰከረ ህዝብ ስሆን በተለያዩ አከባቢዎች ግጭቶች ስነሱ በባህሉ የማስታረቅ ልምድ ያለው ታላቅ ህዝብ ነው።
በአሁኑ ጊዜም በጃርሶ ለሃይተና በናላያ ሰገን ታራጋሜ ሕዝብ መካከል የተከሰተው ችግር የኮንሶን ህዝብ የማይወክል ማንንም ልኮንነው የምገባ ተግባሪ መሆኑን፤ እኛ የኮንስ ዞን የመንግስት ሠራተኞች እና አመራሮች ዛሬ ማክሰኞ 13/09/2016 ዓ.ም በጋራ ባደረግነው ወይይት በመግባባት የምከተሉትን ባለ ሰባት ነጥቦች የአቋም መግለጫ አውጥተናል።
- 1. በጃርሶ ለሐይቴና በናላያ ሰገን ታራጋሜ ሕዝብ መካከል የተከሰተዉ ግጭት የኮንሶ ባህልና እሴት የናዳ እንዲሁም የኮንሶ ህዝብ የማይወክል በመሆኑ እኛ የኮንሶ ዞን ማዕከል ፓብሊክ ሰርቫንትና አመራሮች ተግባሩን በአጽኖት እናወግዛለን!
- 2. በጃርሶ ለሐይቴና በናላያ ሰገን ታራጋሜ ሕዝብ መካከል የተከሰተዉ ግጭት መንስኤ የሆኑት እንዲሁም አንድ ቤተሰብ በሆነ ህዝብ መካከል አለመግባባት በመፍጠር ለንብረት ዉድመት ምክንያት የሆኑ አካላት ጥንቃቄ በተሞላበት አኳሃን ተጠርጣሪዎችን ለሕግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን!
- 3. የተከሰተዉ ግጭት ዳግም እንዳያገረሽ ከምንጩ ለማድረቅና የህገዝብ ለህዝብ ግኑኝነት እንድጠናከር ወንድም እህት የነበረው የህብረተሰባችን ባህል ያከበረ እና ያጠናከረ እንድሁም እንዲንረዳዳ የማቀራረብ ስራን ለመስራት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ቃል እንገባለን!
- 4. በማህበራውዊ ሚዲያ የጥላቻ ንግግሮችና የኮንሶን ገጽታ የሚያጠለሹ፣ በወንድሞች መካከል መጠራጠርና አለመግባባትን የሚፈጥሩ ግለሰቦች በጥብቅ እያወገዝን ችግሮች ካሉ በመቀራራብ ለመፍታት ቃል እንገባለን!
- 5 ግጭቶች ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት አዝማሚያ በመገምገም የግጭቱ ቀድሜ ትንተና በማድረግ እንድሁም ህዝቡን ለማወያየትና የመከልከል ስራን ለመስራት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን!
- 6 በአጎራባች ዞኖች መካከል በየጊዜው የሚከሰቱ የዝርፊያ እና ህይወት የማጥፋት እና በኮንሶ ዞን ውስጥ በህዝቡ መካከል ተሰውረው በእኩይ ተግባር የተሰማሩ ዘራፊዎች እና የግጭቱ ጠማቅዎች እንድሁም ወንበዴዎች ለህግ እንዲቀርቡ ከወንድም ኧሌ ህዝብ ጋር ለመስራት ቃል እንገባለን!
- 7 በአሁኑ ጊዜ የወደሙ ንብረት አውዳሚው አካል ራሱ እንድተካ የተደረግው የመንግሥት አቅጣጫ እየደገፍን በቀጣይ ይህንን አሰራር ህግ ሆኖ እንድጸድቅ ለኮንሶ ዞን ም/ቤት እንድቀርብ አበክረን እንጠይቃለን!
መረጃ
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ግንቦት 13/2016ዓ.ም






