More
በርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የተመራ የክልሉ ልዑክ በወላይታ ዞን ዱጉና ፋንጎ ወረዳ በአርሶ አደሮችና በወጣቶች በክላስተር እየለማ ያለውን የበልግ በቆሎ ማሳ ጎበኙ።




የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በወረዳው በሚገኙ 160 አርሶ አደሮች በ102 ሄክታር ማሳ ላይ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና በሰብል ምርት ገበያን ለማረጋጋት እየሰሩ እንደሆነ ተዟዙረው ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተደድሩ በቀጣይ በዞኑ የሚገኙ የኢንዳስትሪ ልማት ሥራዎችንም ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በምልከታው ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ ኮምሽነር ፍስሃ ጋረደው የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላን ጨምሮ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የግብርና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ለጥፏል።
ግንቦት 12/2016 ዓ.ም







