የከተራ በዓል በኮንሶ ዞን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፣

የከተራ በዓል በኮንሶ ዞን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፣

በበዓሉ ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው በመነሳት በምእመናን ታጅበው በደማቅ ሀይማኖታዊ ስርአት ወደ ጥምቀተ ባህሩ ስፍራ ተጉዘዋል።

በበዓሉ ለምእመናኑ መንፈሳዊ መልእክት ያስተላለፉት የኮንሶ ዞን ወረዳዎች ቤተ ክህነት አስተዳዳሪ ቀሲስ ኤልያስ ቹቹ በአሉ ክርስቶስ ወደ ዮሐንስ ሄዶ በመጠመቁ ትህትናን የምንማርበት ነው ያሉ ሲሆን፣ በዓሉን ስናከብር ፈጣሪ ዓለማችንን፣ ሀገራችንን ብሎም አከባቢያችንን እንዲጠብቅልን በመማጸንና በፍጹም መንፈሳዊ ምግባር ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በበአሉ የታደሙት የካራት ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ያቤሎ ኩሴ ሀገራችን የብዝሀ ባህል ቋንቋ እና ሀይማኖት መገኛ መሆኗን እና የጥምቀት በዓልም በዩኒስኮ ከተመዘገቡ ሀገራዊ ቅርሶች አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ከሀይማኖታዊ ስርዓትነቱ እና ማህበራዊ ትስስርን ከማጠናከሩ ባሻገር ሀገራችን በዓለም ከፍ ብላ እንድትታይ ያደረገ ታላቅ በአል ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ በበኩላቸው በዓሉ ከመንፈሳዊ ስርዓትነቱ ባሻገር በርካታ ማህበራዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ምእመኑ በዓሉን ሲያከብር ሰላሙን በመጠበቅ እና በመረዳዳት እንዲሆን ጠይቀዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገልገሎ ገልሾ ይህ ታላቅ በዓል ሀገራችን በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው ቅርሶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚከበር ነው ብለዋል።

አቶ ገልገሎ አክለውም በዓሉ በርካታ ቱሪስቶች የሚጎበኙት በመሆኑ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ገልጸው በዓሉ ከኃይማኖታዊ ፋይዳው ባሻገር ትህትናን እና መረዳዳትን የሚያስተምር በመሆኑ እንደተለመደው ምእመኑ በመተባበር እና በፍቅር እንዲያከብረው ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

ጥር 10/2017 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *