ኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ከሰዓት ውሎው የ6 ወራት የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሪፖርት አድምጦ ውሳኔ አሳለፈ።

የዞኑ ፋይናንስና በጀት ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ የተከለሰ የ2016 የበጀት ረቂቅ አዋጅ አቅርቦም ፀድቋል።


የከፍተኛ ፍ/ቤት አፈፃፀም ሪፖርት አበረታች ነው ያለው አስተያየት ሰጪ ምክር ቤት አባላቱ፣ ለታችኛው መዋቅሮች ድጋፍና ክትትል ከዚህ በበለጠ መጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

ህዝብ መካከል ልዩነቶችን የሚፈጥሩ ጉዳዮች ዙሪያ መነጋገርና መግባባት ያስፈልጋል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ ልዩ ትኩረት ለሚሹ ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሙሃመድ ቃውያ በተነሱ ሀሳቦች ምላሽና ማብራሪያ በሚሰጡበት ወቅት እንደገለፁት በተለያዩ መዋቅሮች የነበረ የሰው ሀይል እንዲሁም የበጀት እጥረት ቢገጥማቸውም፣ ለታችኛው መዋቅር በተቻለ መጠን በቁሳቁስ በመደገፍ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አስረድተዋል።

የተሻሻለው የበጀት ረቂቅ አዋጅ በዞኑ ምክር ቤት የመንግስት ሀብትና በጀት ፋይናንስ ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ገረሙ ካይሲሞ ቀርቦ ምክር ቤቱ አስተያየት ሰጥቶበት የበጀት ረቂቅ አዋጁን በሙሉ ድምጽ አፅድቀዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ የቀሪ 100 ቀናት አካል የሆነው “አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ” በሚል አጀንዳ ዙሪያ ገለፃ አድርገው ምክር ቤቱ አስተያየት ሰጥተውበት በትኩረትና ንቅናቄ ለመስራት አቅጣጫ አስቀምጧል።

በመጨረሻም የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ የተከበረው ምክር ቤት ለወከሉት ህዝብ አለኝታ በመሆን ዘላቂ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከዚህ በበለጠ ወደ ህዝቡ በመቅረብና ችግሮቹን ለይቶ ለመፍታት እንዲሰሩ መክረው፥ ከአሉባልታ በፀዳና ተጨባጭ በሆኑ መረጃዎች ላይ በመነሳት አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን ማረምና ማገዝ እንዲችሉ መክረዋል።

ምክር ቤቱ የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ እና በ2016 በጀት ግማሽ አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥተው፥ 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሰላም አጠናቋል።

መረጃው
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሚያዝያ 01/2016 ዓ/ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *