የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ በልማትና በሠላም ዕሴት ግንባታ ዙሪያ፣ ከዞኑ የተለያዩ መዋቅሮች የተወጣጡ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ነጋዴው ማህበረሰብ እንዲሁም ከተለያዩ ማህበራዊ መሠረት ከተወጣጡ አካላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በዞኑ ጥያቄ ወቅት የባከነው የልማት ስራን ለመካስ የዞኑ አመራሩን ጨምሮ ሁሉም ልረባረብ ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ በልማትና በሠላም ዕሴት ግንባታ ዙሪያ፣ ከዞኑ የተለያዩ መዋቅሮች የተወጣጡ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ነጋዴው ማህበረሰብ እንዲሁም ከተለያዩ ማህበራዊ መሠረት ከተወጣጡ አካላት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ለመድረኩ ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የህዝባችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለማዳመጥ በአካል በመገኘታችሁ እናመሰግናለን ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጥላሁን ከበደ እንደገለፁት የኮንሶ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ ታታሪ፣ የጽናትና የትጋት ተምሳሌት የሆነ በተፈጥሮ ጥበብ አካባቢውን በመጠበቅ በዓለም የተመሰከረለት እንዲሁም ድንቅ ባህላዊ ዕሴት ያለው ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮንሶ ህዝብ ከክልላችን አልፎ በአዲስ አበባ በጠቅላይ ሚኒስትር በሚከናወኑ ልማታዊ ተግባራት ላይ እየተሳተፈ የሙያና የክህሎት ባለቤት መሆኑን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በዞኑ ጥያቄ ወቅት የባከነው የልማት ስራን ለመካስና በወቅቱ ያጋጠሙ ሰብዓዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ቀውሶችን ለመካስ የዞኑ አመራሩን ጨምሮ ሁሉም ልረባረብ ይገባል ብለዋል።

ክልላችን የሠላም፣የመቻቻል፣የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ያሉን በርካታ ፀጋዎችን ወደ ሀብት ለመቀየር ውስጣዊ አንድነት ወሳኝነት አለው ያሉት አቶ ጥላሁን፤ክልላችን ግጭትን የሚፀየፍ ቱባ ባህሎች የሚገኙባት ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ስለ ሠላም በመስበክ ሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች የተጣለባቸውን አደራ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ፀጋዎቻችንን በአግባቡ አሟጠን እንዳንጠቀም ለተ ቀን የሚተጉ የግጭት ነጋዴዎች አልጠፉም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጥላሁን፤ፈተናዎችንና ወቅታዊ ችግሮችን በመጋፈጥ የውስጥ አንድነትን ማጠናከር ያስፈልጋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን በሚመለከት የክልሉ መንግስት አጽንኦት ሊሰጣቸው ይገባል ብለው ያነሱት ጉዳዮች መካከል የመብራት መቆራረጥና መጥፋት ችግር እንዲሉም ተደራሽነት ችግርን መቅረፍ፣የካራት ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅን ወደ ፖሊ ቴክኒክ ለማሳደግ፤

የካራት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ወደ ሪፈራል ሆስፒታል ለማሳደግ፣ይገነባሉ የተባሉ የጎበዞች ትምህርት ቤት እና ዩኒቨርስቲ ግንባታ፣ከሠገን ከተማ-ካራት መንገድ፣ ከካራት-ከና-ፋሻ መንገድ፣ከና ወረዳን ከቴልተሌ ጋር የሚያገናኝ መንገድ ላይ ድልድይ ግንባታ፣የ2008 የሠራተኞች ደመወዝ ክፍያ ትኩረት የሚሹ የረጅም ጊዜ የህዝባችን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ናቸው ሲሉ ጠይቀዋል።

ከሠላም ዕሴት ግንባታ ጎን ለጎን ልማታዊ ስራዎችን እያከናወንን እንገኛለን ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ ካራት ከተማ የዞኑ መዲና ከመሆኑም በተጨማሪ የክልሉ መቀመጫ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ወቅት ያለመጠናቀቅ፣ በከተማው የሚገኙ የክልል ተቋማት ሠራተኞች እንዲሁም የከተማው ማህበረሰብ ያለ ውሃና መብራት መኖር አለመቻላቸውን የሁልጊዜ እሮሮ ድምፃችንን እያሰማን ቢሆንም ምላሽ መዘግየቱን ተናግረዋል።

ህዝብን ያላሳተፈ ሠላምና ልማት ዘላቂ አይሆንም ያሉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገብረ መስቀል ጫላ፤መንግስትና ህዝብ አንድ ሲሆን ሠላምና ልማት የማይረጋገጥበት ምክንያት አይኖርም ብለው በአንድ ጀምበር የሚረጋገጥ ልማት በለመኖሩ ተደጋግፈን በመስራት ደረጃ በደረጃ ልማቶችን ለማሳካት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አንድነታችሁን ከመቼውም በላይ ማጠናከር ይጠበቅባችኋል ያሉት አቶ ገብረ መስቀል፤አመራሩ የፓርቲውን ዓላማና መርሆዎችን ወደ ህዝቡ የማስረጽ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ያሉት ሲሆን ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር ከአጎራባቾቻችሁ ጋርም ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ መትጋት ይጠበቅችኋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የሚነሱ የህዝባችን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የህዝቡ ጥያቄዎች በመሆናቸው በጥያቄዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ፈጥረን ጥያቄዎቹ ምላሽ የሚያገኙበት አግባብ መፍጠር በመደጋገፍና በመተባበር መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ህዝቡ መካስ ያለባቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ በማለት የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጥላሁን፤የኮንሶ ህዝብ የመቀየር በቂ አቅም ያለው ህዝብ በመሆኑ ያለ ምንም ልዩነት የውስጥ አንድነትን በማጠናከር ህዝቡን መካስ ያስፈልጋል ሲሉ አስገንዝበው ያሉ ጥያቄዎችን እንደየ ደረጃቸው ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ምላሽ ለመስጠት ትኩረት ሰጥተው ዕቅዶች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር የተገቡ ስራዎች መኖራቸውን አስገንዝበዋል።

ከላይ የሚወርዱ ኢንሼቲቮችን በሚገባ ለመፈፀም የአመራሩ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ጥላሁን፤አመራሩ ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት ያልተሠሩባቸው ኢንሼቲቮች ትኩረት በመስጠት ህዝቡን መካስ ይጠበቅበታል ሲሉም አሳስበዋል።

በመጨረሻም ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች የዞኑ መንግስት ላደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ግንቦት 04/2017 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *