ፓርቲው ክልሉን ሊያሻግር እንደሚችል በሕዝቡ ዘንድ አመኔታ ተፈጥሯል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ ተናገሩ።

ፓርቲው ክልሉን ሊያሻግር እንደሚችል በሕዝቡ ዘንድ አመኔታ ተፈጥሯል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ ተናገሩ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ 2017 ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ በደቡብ ኦሞ ዞን ቱርሚ ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በፖለቲካና አቅም ግንባታ፣ አደረጃጀት፣ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ፣ ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ፣ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር እንዲሁም ሀብት ልማትና አስተዳደር ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባዉዲ ፓርቲው ሰፊ የማህበራዊ መሠረትና የሕዝብ ቅቡልነት ከመፍጠሩም በላይ ክልሉን ሊያሻግር እንደሚችል በሕዝቡ ዘንድ አመኔታ መፍጠር እንደቻለ ገልፀዋል።

በተጠናቀቀዉ የበጀት ዓመት ባለፉት አምስት ዓመታት ዉስጥ ያልተሰሩ ስራዎችን በሰዉ፣ በአመለካከት እና በተቋማት ላይ መስራት እንደተቻለ አቶ አለማየሁ ጠቅሰዋል።

የሲቪክ ማህበራትን ፓርቲው ላነገባቸዉ ዓላማዎች በማዋል በኩል ያሉ ክፍተቶችን ማስተካከል እንደሚገባ ጠቁመው መቅደምን ማዕከል ባደረገ የሚዲያ ስራ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም የገዢ ትርክት ግንባታን ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ገበየሁ አንዳንድ መዋቅሮች ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ችግሮችን አጀንዳ በማድረግ የሚጠመዱበት አዝማሚያ ሊታረም እንደሚገባ አሳስበዋል።

እያንዳንዱ የፓርቲው አመራሮች በግልፅ በተቀመጡ መስፈርቶች ብቻ እንደሚመዘኑ ገልፀው የፓርቲውን የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን እንደ ፓርቲው የዉስጥ ኦዲተር በመቁጠር በትብብር መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

2017 የአከባቢ ምርጫና የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤን ጨምሮ ትላልቅ ተግባራት የሚከናወኑበት ዓመት እንደመሆኑ መላዉ የፓርቲዉ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ከመቼዉም ጊዜ በላይ በላቀ የመፈፀም ቁመና ላይ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።

በመድረኩ የ 2017 ዓ.ም ጠቋሚ ዕቅድ፣ የምርጫ፣ የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ እና የክልል ማዕከል የፓርቲ ህንፃ ግንባታን ሀብት አሰባሰብ በተመለከተ መነሻ ሰነዶች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

በመድረኩ የክልል ማዕከል ፓርቲ አመራሮች፣ የክልል ማዕከላት የመሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢዎች፣ የ 12ቱም ዞኖች አስተባባሪዎች እና የወጣቶችና ሴቶች ሊግ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የክልሉ ፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘግቧል።

ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *