የትራኮማ በሽታን ለማስወገድ በሚደረገውን ጥረት የኮሚኒኬሽን ተቋም ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተጠቆመ።

የአይን ማዝ በሽታን ለመከላከልና ህብረተሰቡን በዘርፉ ለማንቃት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸዉ ተጠቁሟል።

ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉ/ቢሮ ጋር በመተባበር ለመንግስት ኮሚኒኬሽን አመራሮችና ለሚዲያ ባለሙያዎች ትራኮማ በሽታን መከላከል ተግባር ዙሪያ መከሩ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ተወካይ አቶ ዮሴፍ አፋማ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጤናዉ የተጠበቀና አምራች ዜጋን ለመፍጠር የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ጉልህ ድርሻ አለዉ ብለዋል።

የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ሀገር አቀፍ ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ሲሳይ በበኩላቸው ተቋሙ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከ40 አመት በላይ በዓይን ጤና ላይ ሲሰራ መቆየቱን አስታዉሰዋል።

በዓለም ከ2 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ የዓይን ጤና ችግር ተጠቂ መሆናቸውን የገለፁት ዶ/ር አለማየሁ፥ ከነዚያ ውስጥ ከ1 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ታማሚዎች የአይን በሽታው በቀላሉ መዳን የሚችል ነዉ ብለዋል።

በመድረኩ ስለ አይን ጤና አጠባበቅና የኮሚኒኬሽን ሚና የሚል ርዕስ ዶ/ር አለማየሁ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን የዜጎቻችን የአይን ብርሃን እንዲጠበቅ ኮሚኒኬሽና ሚዲያው ህዝቡን ማንቃት ይጠበቃል ብለዋል።

በኦርቢስ ኢንተርናሽናል ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ህንረተሰቡን በሚዲያ ማንቃትና ማስተዋወቅ፣ በህብረተሰቡ ፆታን ያማከለ ግንዛቤ መፍጠር የሚሉ ርዕሶች በአቶ ታደሰ ዳታ እና በአቶ ተመስገን ቃባቶ የቀረበ ሲሆን ልማታዊ ጋዜጠኝነትና ጤና ተቋም በሚል ርዕስ የጋሞ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ አዲሱ አዳሙ (ዶ/ር) ቀርቧል።

ከ12 ዞኖች የተውጣጡ የኮሚኒኬሽን አመራርና ባለሙያው በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሀሳብ አስተያየት ሰጥተዋል።

የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ካንትሪ ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ሲሳይ እንደገለፁት የአይን ማዝ (ትራኮማ) በስፋት ከሚስተዋልባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ጠቁመው፥ የግልና የአከባቢ ንፅህናን በአግባቡ በመጠበቅ በሽታዉን መከላከል ይቻላል ብለዋል።

ለትራኮማ አጋላጭ ምክንያቶችንና መፍትሔዎች ላይ የኮሚኒኬሽንና ሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች ለማሕበረሰቡ ተገቢዉን መረጃ በማስተላለፍ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ዶ/ር አለማየሁ ጥሪ አቅርበዋል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ተወካይ አቶ ዮሴፍ አፋማ በማጠቃለያቸው ኮሚኒኬሽንና ሚዲያ አመራሩ ከቃል በላይ በተግባር የሚገለፅ በመሆኑ የአይን ማዝ በሽታን ማጥፋት በርትተን ልንስራ ይገባል ብለዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

ሐምሌ 04/2016

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *