greenlegacy2018

“ተስፋን እንትከል!” በሚል መሪህ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ መለጋ ዱጋያ ቀበሌ በይፋ ተካሂዷል፣

‎ካራት:ሐምሌ ።27/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

በ2018 ዓ.ም “ተስፋን በጋራ እንትከል!” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ የቡና ክላስተር በሆነችው መለጋ ዱጋያ ቀበሌ በይፋ ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና የኮንሶ ዞን ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች፣ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የፀጥታ አካላትና በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች በንቃት ተሳትፈዋል።

በቡና ክላስተር በሆነው መለጋ ዱጋያ ቀበሌ በተካሄደው መርሃ ግብር፣ የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የአፈር ለምነትን ለማስጠበቅ፣ የደን ሽፋንን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር ያለው ወሳኝ ሚና ተጠቅሷል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙ ኃላፊዎች የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁ ተከታታይ እንክብካቤና ክትትል ሊደረግላቸው እንደሚገባ በማሳሰብ፣ የአረንጓዴ አሻራ ውጤታማነት የሚረጋገጠው በተተከሉት ችግኞች ፅድቀትና ቀጣይ እንክብካቤ መሆኑን ገልጸዋል።

በዕለቱም በመላው የኮንሶ ዞን ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች በተዘጋጁ የተከላ ቦታዎች የክልልና መላው ህብረተሰብ በሰፊው በመሳተፍ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን በስኬት በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

በጊያ ግና

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *