የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በገቢ አሰባሰብ በክልሉ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸልሟል፣

የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በገቢ አሰባሰብ በክልሉ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸልሟል፣

የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው አመርቂ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ዞኖች መካከል 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸልሟል።

ይህ ውጤት የመምሪያው ብቻ ሳይሆን የዞኑ አመራር፣ የተለያዩ ተቋማት፣ የግብር ከፋዮችና የህብረተሰቡ ተሳትፎ በጋራ ያመጣው ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በአርባ ምንጭ ከተማ ባካሄደው የምክክር መድረክ ላይ ለተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መዋቅሮችና ባለሙያዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።

በዚሁ መርሃ ግብር የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ በገቢ አሰባሰብ ዘርፍ ባስመዘገበው ከፍተኛ አፈጻጸም 3ኛ ደረጃን በመያዝ እውቅና ያገኘ ሲሆን፣ ሽልማቱን የመምሪያው ኃላፊ አቶ ካሳሁን ገረመው ተቀብለዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ በገቢ አሰባሰብ ሥራው ላይ የተቋሙን አቅም ለማጠናከር፣ የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ የሰጡት ቁርጠኛ ክትትልና ድጋፍ ፣ ከዚህም ባሻገር በዞኑ መላው አመራሮች በገቢ አሰባሰብ ሥራው ላይ የሰጡት አቅጣጫ፣ ድጋፍና ቅንጅታዊ አሠራር ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ አድርጓል።

በውጤቱም ከክልሉ የሪጂዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደሮች መካከል የዲላ ከተማ ገቢዎች መምሪያ 1ኛ ደረጃን ይዞ ሲሸለም፣ ከዞኖች መካከል የጋሞና አሪ ዞኖች 1ኛ፣ የደቡብ ኦሞና ወላይታ ዞኖች 2ኛ፣ የኮንሶና ጌዴኦ ዞኖች ደግሞ 3ኛ ደረጃን በመያዝ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ ያገኘው ይህ እውቅና በተቋሙ የተደራጀ የገቢ አሰባሰብ ሥራ፣ የግብር ከፋይ ግንዛቤ ማሳደግ፣ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓትን ማሻሻልና የተሻለ አፈጻጸም ለማምጣት የተደረገውን ጥረት የሚያመላክት ነው።

በመድረኩ በተጨማሪም የ2019 በጀት ዓመት የሥራ ግብ ስምምነቶች ተፈርመው የቀጣይ ዓመት የገቢ አፈጻጸምን በተሻለ ደረጃ ለማሳካት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

ካራት፡ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *