ችግኞችን በአግባቡ በመንከባከብ፣ አዳዲስ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎችን በማስፋፋትና በአዲሱ በጀት ዓመት ከዕቅድ በላይ ለማከናወን ቅድሜ ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ ጉራሾ ጎስኬ አስታወቁ::

ችግኞችን በአግባቡ በመንከባከብ፣ አዳዲስ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎችን በማስፋፋትና በአዲሱ በጀት ዓመት ከዕቅድ በላይ ለማከናወን ቅድሜ ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ ጉራሾ ጎስኬ አስታወቁ::

ካራት፦ ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም;(ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን )

የኮንሶ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጉራሾ ጎስኬ በዞኑ ሰገን ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ የሰገንዶዴ: ብርብርሳ፣ ሉልቱ እና የመገርሳ የችግኝ ጣቢያዎችን በመጎብኘት፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዘላቂ ውጤት እንዲያስገኝ ከተከላ በኋላ የችግኞች እንክብካቤና የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎችን ማስፋፋት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ መመሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ጉራሾ በጉብኝቱ ወቅት፣ ለዘንድሮው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከተዘጋጁት በተጨማሪ ያልደረሱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ችግኝ መኖሩን ግልፀው እነኝህ ችግኞች እንዳይባክኑ በተገቢው እንክብካቤ በማሳደግ ለቀጣይ መሄር ዝናብ ወቅት የተከላ መርሃ ግብሮች ዝግጁ እንዲሆኑ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ከዚህ ባለፈም በየቀበሌው አዳዲስ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎችን በማቋቋም የችግኝ አቅርቦትን ማሳደግና በቀጣይ ዓመታት ከተያዘው ዕቅድ በላይ ውጤት ለማስመዝገብ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በተለይም የቡና፣ የፍራፍሬና የተለያዩ የደን ችግኞችን በስፋት በማፍላት የአካባቢውን አረንጓዴ ሽፋን ከማሳደግ ባሻገር ለአርሶ አደሮች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በርሻ ኦላታ በበኩላቸው፣ የተሰጡት አቅጣጫዎች የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎችን በተሻለ ደረጃ ለማደራጀትና በቀጣይ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከዕቅድ በላይ ውጤት ለማስመዝገብ መሠረት እንደሚሆኑ ገልጸው አከባቢውን ባማከለ መልኩ ማፍላት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የብርብርሳ ቀበሌው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሽ ዘውዴ፣ ከአመራሩ የተሰጡትን መመሪያዎች ተግባራዊ በማድረግ ያሉትን ችግኞች በአግባቡ እንደሚንከባከቡ፣ አዳዲስ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎችን እንደሚያስፋፉ እና በቀጣይ ዓመት ከተያዘው ዕቅድ በላይ ለማሳካት በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዘላቂ ስኬት የሚረጋገጠው ችግኞችን በመትከል ብቻ ሳይሆን በማሳደግ፣ በመንከባከብና የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎችን በቀጣይነት በማስፋፋት መሆኑን አመራሮቹ የገለጹት ስሆን በአከባቢው የሚገኙ የቀድሞ ቡና ችግኝ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል።

በጊያ ግና

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *