የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮንሶ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር ለመንግስት ሰራተኞች በቴክኖሎጂ የታገዘ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ለማዳረስ የውል ስምምነት ተፈራርሟል።

የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮንሶ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር ለመንግስት ሰራተኞች በቴክኖሎጂ የታገዘ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ለማዳረስ የውል ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱ ሰራተኞች የብድር፣ የቁጠባ፣ የሲቢኢ ብር (CBE Birr) እና ሌሎች ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንክ በአካል ሳይሄዱ ከያሉበት ሆነው እንዲጠቀሙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ አሰራር የገንዘብ ዝውውር፣ የቁጠባ እና የብድር አገልግሎቶች በቀላልና ፈጣን ሁኔታ የሚሰጡ ሲሆን፣ ከወረቀት አሰራር ነፃ የሆነ ዘመናዊ የፋይናንስ ሥርዓት በመፍጠር የአገልግሎት ቅልጥፍናና ግልጽነትን እንደሚያሳድግ ተጠቁሟል።

በስምምነቱ መሠረት ሰራተኞች ከ1 እስከ 4 ወር ደመወዝ ድረስ ብድር ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ደመወዛቸው በሲቢኢ ብር አማካኝነት መከፈል እንዳለበት ተገልጿል።

የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሳዬ ገልገሎ፣ አገልግሎቱ ለመንግስት ሰራተኞች የገንዘብ እጥረትን ለማቃለልና የፋይናንስ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበኩሉ ወደፊት ተጨማሪ የብድርና የፋይናንስ አገልግሎቶች እንደሚቀርቡ አስታውቋል።

በመጨረሻም የተፈረሙት ስምምነት በዞኑ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን በማስፋፋት ለመንግስት ሰራተኞች ተደራሽ፣ ፈጣንና ዘመናዊ አገልግሎት ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

መረጃው፦ የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በጊያ ግና

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *