የኮንሶ ዞን ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ በልማት ማስፋፊያ አከባቢ የሚገኙ ህገወጥ ይዞታዎችን ህጋዊ ስርአት ለማስያዝ በተወሰነው የመስተዳድር ምክር ቤት ውሳኔ ዙርያ የውይይት መድረክ አካሄደ

የኮንሶ ዞን ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ በልማት ማስፋፊያ አከባቢ የሚገኙ ህገወጥ ይዞታዎችን ህጋዊ ስርአት ለማስያዝ በተወሰነው የመስተዳድር ምክር ቤት ውሳኔ ዙርያ የውይይት መድረክ አካሄደ።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ መሳይ አሰፋ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የከተማችንን ዕድገት ማፋጠን ይቻል ዘንድ ፕላን መውረዱ አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በመድረኩ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የዞኑ ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ታምሩ ቦያ የመድረኩን ዓላማና

አስፈላጊነት፣ ልዩ ልዩ ግቦችንና ግቦቹን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራትን፣ እንደዚሁም የመስተዳድር ምክር-ቤቱን ውሳኔዎች በዝርዝር አቅርበዋል።

1,566 ፋይል በህገወጥ ግንባታነት የተመዘገበ መሆኑንም ያብራሩት አቶ ታምሩ ከተሞችን በፕላን ለመምራትና ህገ-ወጥ ግንባታዎችን በዘላቂነት ለማስቆም፣ ብሎም የከተሞችን የገቢ አቅም ለማሳደግ ለነዋሪዎች ምቹ የሆነ ከተማን መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

በካራት ከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ የከተማውን ፕላን በዝርዝር አቅርበው ማብራሪያ ሰጥተውበታል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም ውሳኔዎቹ ተግባር ላይ በሚውሉበት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባል ያሉ ሲሆን፣ ካለው የመሬት ችግር አንጻር የውሳኔው ተግባራዊነት ጥሩ መፍትሄ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የድጋፍ ቡድኖችም አተገባበሩን በቅርበት የሚከታተሉ መሆኑን ገልጸው፣ ስራው በፍጥነት እና በጥንቃቄ መሰራት እንዳለበትና ከገቢ ብሎም ከተማው በፕላን እንዲመራ ከማስቻል አንጻር ይህ ትልቅ እድል ነው ሲሉ አስረድተዋል።

የዞኑ ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኩንዳርታ ኩታዬ በበኩላቸው የስራው ባለቤት እንደመሆናችን ከስጋት ወጥተን በመናበብ እና በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ መሳይ አሰፋ ስራውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚገባ ገልጸው ስራዎች እየተሰሩ ሳለ ለሚነሱ ጥያቄዎች በጋራ በመሆን ምላሽ እየሰጠን የምንሄድ ይሆናል ያሉ ሲሆን፣ ለተግባራዊነቱ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊንቀሳቀሱ ይገባል ሲሉ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *