ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከተስፋ ጭላንጭል ወደ ሚጨበጥ ብርሃን

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከተስፋ ጭላንጭል ወደ ሚጨበጥ ብርሃን የሚያሻግረን ታላቅ ፕሮጀክት በመሆኑ ሁሉም ሰው የዜግነት ግዴታውን ሊወጣ ይገባል-የተከበሩ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለድጋፍና ክትትል ከመጣው ቲም ጋር ዞናዊ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የመጨረሻ ምዕራፍ የቦንድ ግዥ ሂደት ያለበትን ደረጃ ገመገሙ።

ዋና አስተዳዳሪው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የሀገሪቱ ዜጎች ኩራት ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን ህዝብ የመቻል አቅም ያሳየ፣ ከተስፋ ጭላንጭልም ወደ ሚጨበጥ ብርሃን የሚያወጣን ታላቅ ፕሮጀክት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የተከበሩ አቶ ገለቦ አክለውም ለግድቡ ግንባታ የሚከናወነውን የቦንድ ግዥ ከሌሎች ልማታዊ የሀብት ማሰባሰቢያ ተግባራት ልዩ የሚያደርገው እንደ ዜጋ አሻራን ከማሳረፍ ባሻገር ቁጣባ በመሆኑ ነው ያሉ ሲሆን፣ ለተቀረው የግንባታው የመጨረሻ ምዕራፍ በንቅናቄ መሳተፍ ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል ዋዳ በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የፓርቲውን እና የመንግስትን ቅቡልነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

ግድቡ የህዝቡን አቅምና የአመራር ስርዓት ከህዝብ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ያሉት አቶ ሚካኤል፤ ብልጽግና ውጤትን በተግባር በማምጣት የሚያምን ፓርቲ በመሆኑ አመራሩ በጉዳዩ ተግባቦትን ፈጥሮ የታች መዋቅሮችን ድጋፍ ማጠናከር ይጠበቅበታል ሲሉ አሳስበዋል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ገረሱ ካታሌ ለግድቡ ግንባታ እየተከናወነ ያለውን የቦንድ ግዥ አስመልክተው ዞናዊ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ተግባሩ ከዞን ጀምሮ እስከ ታች መዋቅሮች በቁርጠኝነት መመራት እንዳለበት አመላክተዋል።

የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሐመር ሐንሻ በበኩላቸው ዕቅዱን ለማሳካት ያሉ ማህበራዊ መሠረቶችን በመለየትና ግንዛቤ በመፍጠር በቁርጠኝነት ልንሠራ ይገባል ብለዋል።

የቦንድ ግዥ ሂደትን አስመልክቶ የዞኑ አስተባባሪዎች መዋቅሮችን ተከፋፍለው እየደገፉ መሆናቸውን የገለፁት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መሳይ አሰፋ ያለንን አቅም አሟጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሰጠንን ድርሻ ማሳካት ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል።

ለድጋፍና ክትትሉ የመጡት አካላት ከችግሮች በላይ ሆነን በመስራት ግድቡን ከዳር ማድረስ እንችላለን ያሉ ሲሆን ለዚህም ከላይ እስከታች የተጠናከረ ቅንጅታዊ አሠራርን፣ እንደዚሁም የመረጃና የሪፖርቶች ልውውጥን ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመጨረሻም የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ገለቦ ተግባሩ ከተያዘለት ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በሚፈለገው ልክ አለመሠራቱን ገልፀው ከዚህ በኋላ ባለው ጥቂት ጊዜ ውስጥ መሠረታዊ ችግሮችን በመለየት፣ ከላይ እስከታች ተግባቦትን በመፍጠር፣ ማህበራዊ መሠረቶችን በማነጋገርና የድርሻቸውን ቆጥሮ በመስጠት ቆጥሮ መረከብ እንደሚያስፈልግ፣ እንደዚሁም ዕለታዊ የግምገማ ስርዓትን መዘርጋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

መጋቢት 04/2017 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *