የኮንሶ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታም በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት፣ በኮንሶ ዞን አስተዳደር እና በልማት አጋሮች መካከል የተፈጠረ የትብብር ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

በኮንሶ ዞን 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም ከተጠናቀቀ በኋላ የልማት ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠላቸው ተገለጸ

በኮንሶ ዞን 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም፣ በሥርዓትና በተሳካ ሁኔታ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ከምርጫው በፊት ሲከናወኑ የነበሩ የልማት ሥራዎች በተጠናከረ አቅም መቀጠላቸው ተገልጿል።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ በቅርቡ በካራት ከተማ እሳሌ ሰፈር የተካሄደውን የኮንሶ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጫ መርሃ ግብር ላይ እንደገለጹት፣ የምርጫው ሰላማዊ አካሄድ እና ስኬታማ መጠናቀቅ በዞኑ የልማት ሥራዎች ላይ የበለጠ ትኩረት ለመስጠት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

ዋና አስተዳዳሪው “ትምህርት የሁሉም ልማቶች መሠረት ነው” በማለት፣ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ዜጎች ለማዳረስ ከፌዴራል መንግሥት እስከ አካባቢ አስተዳደሮች ድረስ የተለያዩ የትምህርት ማሻሻያ ኢኒሼቲቮች እየተተገበሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ “አንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ” እና የሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ከእነዚህ ተጠቃሽ ፕሮግራሞች መካከል መሆናቸውን አስረድተዋል።

በአባቶች ቡራኬና በኮንሶ ባህላዊ ኪነ-ጥበብ ትርኢት የተከፈተው የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጫ መርሃ ግብር፣ በዞኑ የትምህርት ዘርፍ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችን የሚያመላክት ተግባራዊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ በንግግራቸው፣ የትምህርት መሠረተ ልማትን ለማጠናከር የመንግሥት፣ የልማት አጋሮችና የማህበረሰቡ የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው፣ የኮንሶ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታም በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት፣ በኮንሶ ዞን አስተዳደር እና በልማት አጋሮች መካከል የተፈጠረ የትብብር ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የሰው ለሰው ድርጅት ተወካይ አቶ ተስፋመድህን ገ/ኪዳን በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተመሳሳይ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እየተገበረ መሆኑን ገልጸው፣ ለፕሮጀክቶቹ ስኬት የመንግሥት ድጋፍና የማህበረሰቡ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙ፣ እንድሁም መሰረድንጋዩን በይፋ ያስቀመጡት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው፣ የኮንሶ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለረጅም ዓመታት ሲጠየቅ የነበረ የኮንሶ ሕዝብ የልማት ጥያቄ መሆኑን ገልጸው፣ ፕሮጀክቱ በትምህርት ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን በመቅረፍ ጥራት ያለው ትምህርት ለቀጣዩ ትውልድ ለማዳረስ የሚያግዝ ተጨባጭ እርምጃ መሆኑን አስታውቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም፣ የኮንሶ ሕዝብ በሀገር በቀል ዕውቀቱ፣ በባህልና በታሪኩ ዓለም አቀፍ እውቅና ያተረፈ ሕዝብ ከመሆኑም በላይ ለሀገሪቱ በርካታ ምሁራንን ያበረከተ ማህበረሰብ መሆኑን ገልጸው፣ የትምህርት ቤቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ሁሉም አካላት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በካራት ከተማ እሳሌ ሰፈር የተቀመጠው ይህ የመሠረተ ድንጋይ፣ በኮንሶ ዞን የትምህርት መሠረተ ልማትን ለማጠናከር፣ ለተማሪዎች የተሻለ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር እና የወደፊቱን ትውልድ በእውቀት ለማብቃት እየተወሰዱ ካሉ የልማት እርምጃዎች አንዱ መሆኑ የገለጸ ስሆን በመርሃግብሩ የክልሉ ፣የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ፣በዞኑ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል ።

መረጃው:

የኮንሶ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ግንቦት 2018 ዓ.ም.

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *