በኮንሶ ዞን ከተያዘው የ90 ቀናት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ዕቅድ ውስጥ የአንድ ወር ተግባራት አፈፃፀም ተገምግሟል

በመንግስትና በፓርቲ መሳካት አለባቸው ተብለው የታለሙ ዕቅዶችን ወደ መሬት ማውረድ እንደሚገባ ተገለጸ፣

በኮንሶ ዞን ከተያዘው የ90 ቀናት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ዕቅድ ውስጥ የአንድ ወር ተግባራት አፈፃፀም ተገምግሟል።

በመድረኩ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ አቶ ደመላሽ ጎንዲሼ ከ90 ቀናት ዕቅድ ውስጥ የአንድ ወር ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርትን ሲያቀርቡ በማዐጠሜ፣ በግብርና ዘርፍ፣ በትምህርት፣ በገቢ፣ በሰው ሀብት ስራዎች እና መሰል ተግባራት የታዩ ደካማ እና ጠንካራ ጎኖችን በማብራራት በተለይ በቅንጅት ከመስራት አኳያ ሰፊ ክፍተት እየተስተዋለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ፣ በሌማት ትሩፋት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት የሌማት ትሩፋት የሀገር መሶብን በምግብ የመሙላት ዓላማን አንግቦ የሚሰራ በመሆኑ በእጅጉ ትኩረት ይሻል ብለዋል።

የሌማት ትሩፋት ስራ ለአራት ዓመታት የታቀደ መሆኑን እና

ከተጀመረ ሶስት ዓመታትን ማስቆጠሩን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው፣ እንደኛ አከባቢ ግን እስከአሁን ይህ ነው የሚባል ለውጥ ስላልተመዘገበ ከዚህ በኋላ በተፈለገው ልክ ሊሰራበት ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ከ90 ቀናት ዕቅድ ውስጥ የወሩን ተግባር አፈጻጸም ግምገማ እያንዳንዱ አስፈጻሚ አካል ወደራሱ በመውሰድ በየቀኑ የሚቆጠር ስራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

ገቢ ላይ መስራት ከችግር መውጣት በመሆኑ ተግባራትን በትኩረት በመምራት በተለይ ለአዲሱ የገጠር መሬት መጠቀሚያና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር ክፍያ ተግባራዊነት ሁሉም የድርሻውን በመወጣት ውጤት ማምጣት እንደሚገባው አሳስበዋል ዋና አስተዳዳሪው።

የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሐመር ሐንሻ፣ የልማት ፍላጎትን ማሟላት የሚቻለው በብድርና በእርዳታ ሳይሆን በራስ አቅም የገቢ አሰባሰብን በማሳደግ ነው ያሉ ሲሆን፥ የዞኑን ወጪ በራስ ለመሸፈን ገቢን በወቅቱ መሰብሰብ ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል ።

ዋና የመንግስት ተጠሪው አክለውም ስራዎችን በመገምገም የሚታዩ ችግሮችን ማረም የሚያስፈልግ በመሆኑ ከገጠር መሬት መጠቀሚያ ግብር ጋር ተያይዞ አርሶ አደሩ በሚጠቀመው መሬት ልክ ግብር እንዲከፍል ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው በግብርናው ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች ጥሩ ሆነው በቴክኖሎጂ ከማዘመን አኳያ ግን

ሰፊ ክፍተት እየተስተዋለ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ ስራዎችን በቁርጠኝነት ወደ መሬት ያለማውረድ፣ እንደዚሁም ተቀናጅቶና ተተክሎ ያለመስራት ክፍተቶች በስፋት ስለሚታዩ ይህን ሁኔታ በፍጥነት ለማረም ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያም በአመራሩ ፈቃድኝነት ላይ የተመሠረተ የደም ልገሳ መረሃ-ግብር ተካሂዷል።

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *