#Ethio_Konso የኮንሶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በቀሪው 60 ቀናት የፓርቲና የመንግስት ዋና ዋና የንቅናቄ ስራዎች ዕቅድ ዙሪያ መክረዋል።
የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫሬ እንደገለጹት ፓርቲው ጠንካራ ሀገረ መንግስትን ለመገንባት በየደረጃ ያሉ ንዑሳን አደረጃጀቶችን ማጠናከርና በተልዕኮው ግንባር ቀደም ማድረግ እንደሚገባ አብራርተዋል።
በኮንሶ ዞን ለአራት ተከታታይ የምርት ጊዜያት በዝናብ እጥረት ምክንያት ምንም ምርት መሰብሰብ አለመቻሉን ያስታወሱት ኃላፊው አሁን ከዝናብ መምጣት ጋር ተያይዞ የተሻለ የግብርና ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገለጸው፣ በግብርና ግብዓት አጠቃቀም ዙሪያ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ሊስተካከሉ ይገባል ብለዋል።
ትምህርት መተኪያ የሌለው ተቋም እንደመሆኑ ሁሉም አመራር ከዚህ ቀደም የወሰደውን ትምህርት ቤቶቹን የማቀፍ ተልዕኮ በትምህርት ዘርፍ እየታየ ያለውን ለውጥ በይበልጥ እንዲጠናከር ተልዕኮውን በትኩረት እንዲወጡ አቶ ተስፋዬ አሳስበዋል።
ለፓርቲ ተቋማዊ ግንባታ ጥንካሬዎችን በማስፋትና ጉድለቶችን በማረም፤ከህዝብ ለሚነሱ አንገብጋቢ ጉዳዮች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የንቅናቄ መድረኮች በመፍጠር፣ የፓርቲውን ዓላማ ለማሳካት በየደረጃ ያሉ ንዑሳን አደረጃጀቶችን ማጠናከርና በተልዕኮው ግንባር ቀደም ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ተስፋዬ አብራርተዋል።
አቶ ተስፋዬ ጨምረው በቀጣይ ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች መካከል የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ፣ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት፣ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሚመለከት ፓርቲውና የመንግስት በቀሪው የ60 ቀናት ውስጥ በትኩረት ለመስራት ከታቀዱ ተግባራት ውስጥ መካተታቸውን አስረድተዋል።
ተግባራት ከላይ እስከ ታች በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመሩ፣በውጤት የታጀበ ወቅታዊ ሪፖርቶች ከታችኛው መዋቅር ተጠናቅሮ በወቅቱ እንዲቀርብ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የዞን አመራሮች፣የከተማ አስተዳደር እና የሁሉም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
መረጃው
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሚያዝያ 28/2015 ዓ/ም







