በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የካራት ክላስተር የክልል ማዕከል”የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት!” በሚል መሪ ሀሳብ ለ4ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አባላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፣
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የካራት ክላስተር የክልል ማዕከል ተስፋ ብርሃን መሠረታዊ ድርጅት “የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት!” በሚል መሪ ሀሳብ ለ4ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አባላት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና በተለያዩ ክዋኔዎች ፍፃሜውን አግኝቷል።
በማጠቃላይ መድረክ ላይ የተገኙት የካራት ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ እንደተናገሩ እንደ ፓርቲ የተያዙ ተሻጋሪና ልዕልና መር ሀሳቦች ተፈፃሚ የሚሆኑት አባሉ አርቆ በማየት እና አልቆ በመስራት ህብረተሰቡን በታማኝነት ማገልገል ሲችል ብቻ ነው ብለዋል።
በመጨረሻም የካራት ክላስተር የክልል ማዕከል ተስፋ ብርሃን መሠረታዊ ድርጅት የብልጽግና ፓርቲ አባላት የብልጽግና ፓርቲን የአምስት ዓመታት ስኬታማ ጉዞ በተለያዩ ዝግጅት አክብረዋል።
መረጃው
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ












