በኮንሶ ዞን ባደረጉት ጉብኝት እጅግ ደስተኞች መሆናቸውን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ገለጹ።

በኮንሶ ዞን ባደረጉት ጉብኝት እጅግ ደስተኞች መሆናቸውን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ገለጹ።

የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የፊታችን ሕዳር 29 የሚከበረውን 19ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ዞኖች በመዘዋወር የተለያዩ ባህላዊ እሴቶችን እና የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።

ወደ ኮንሶ ዞን የመጡ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በነበራቸው ቆይታ የተለያዩ ቦታዎች የጎበኙ ሲሆን፣ ከአቀባበል ጀምሮ በነበረው ሁኔታ ብሎም ባዩት ነገር እጅግ ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።

More Photos Konso Zone

በኮንሶ ዞን የሚዲያ ቱር ካደረጉት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መካከል OBN፣ Addis media network፣ ኢዜአ፣ Wolayta Tv፣ አፋር ብዙሃን መገናኛ እና ጋምቤላ ብዙሃን መገናኛ ይገኙበታል።

ባለሙያዎቹ በኮንሶ ዞን ጉብኝታቸው በዩኔስኮ አለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገቡ አምባ መንደራትን፣ ልዩ ልዩ ሞራዎችን ፣ የትውልድ መቁጠሪያ የሆኑትን ኦላህታ፣ ቆርማ ፣ፓሌታ፣ ሀርታ(ባህላዊ ኩሬ)፣ ኒውዮርክ፣ ካዋታ(እርከን) እና የግብርና ሥራዎችን የጎበኙ ሲሆን የኮንሶን ባህላዊ መጠጥ የሆነውን ጨቃም አጣጥመዋል።

በዞኑ ያሉ የቱሪዝም አቅሞች እና እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ብሎም በርካታ የቱሪስት መስህቦች የቀደሙ ትውልዶች ከእኔነት ይልቅ እኛነትን የሕይወት ልምምዳቸው አድርገው እንደኖሩ የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።

የመገናኛ ብዙሃኑ ባለሙያዎች በዞኑ ባደረጉት ጉብኝት ደስተኛ በመሆናቸው በቀጣይ በዞኑ ያሉ የቱሪዝም አቅሞችን እና እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን ለማስተዋወቅ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ ነው

ሕዳር 08/2017 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *