
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የ3 ቀናት የድጋፍና ክትትል ማጠቃለያ ግብረመልስ ለኮንሶ ዞን ምክር ቤት ሰጠ።
የዞን፣ የወረዳና ቀበሌያት ምክር ቤቶችን አፈጻጸም በማየት በጥንካሬ የታዩትን ማስቀጠልና በጉድለት የታዩትን ለማሻሻል ያለመ ምልከታ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የድጋፍ እና ክትትል ቡድኑ አስታወቀ።
በግብረ መልሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ አልማዝ ዘውዴ እንደገለፁት በዞኑ ሁለት መደበኛ ጉባኤዎችን ማካሄድ፣ የጉባኤ አባላት ተሟልቶ መገኘት፣ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ወደራስ በመውሰድ በህዝብ ተሳትፎ ጠንካራ ስራዎች መሰራታቸውን እንዲሁም የኮሚኒኬሽን መረጃዎች በአግባቡ መደራጀታቸው በጥንካሬ የተመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ወ/ሮ አልማዝ አክለውም በቀበሌ እና በወረዳዎች አከባቢ የጉባኤ ክፍተቶች መኖራቸው፣ 2 ቀበሌዎች ምንም አይነት ጉባኤ አለማካሄዳቸው፣ የህዝብ አስተያየት መስጫ መድረክ አለመካሄዱ እንደክፍተት የታዩና ሊሻሻሉ የሚገባቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።
በክልሉ ምክር ቤት የተቋማት ስራዎች ቁጥጥር እና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ጴጥሮስ ኩማንቴ በበኩላቸው ለክልሉ መጠናከር ከቀበሌ ጀምሮ ያሉ የተግባራት አፈጻጸሞች ለስኬቱ ቁልፍ ናቸው ሲሉ ተናግረው የኮንሶ ዞን ምክር ቤትም የቆየ ምክር ቤት እንደመሆኑ መጠን በተግባራቶቹ ለሌሎችም ሞዴል መሆን ይጠበቅበታል ሲሉ መክረዋል።
ጥንካሬዎች እንዳሉ ሆነው የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ያለማድረግ፣ ምርጥ ተሞክሮ ያለመቀመር፣ የተስተዋሉ ክፍተቶችን መሙላት፣ ህግ የማውጣት፣ የአስፈጻሚ አካላትን የመቆጣጠርና ህደቱ ጠንክሮ ልቀጥል ይገባል ብለዋል አቶ ጰጥሮስ።
የክልሉ ምክር ቤት የህግ ባለሙያ አቶ ደሳለኝ ደነበ በበኩላቸው በጠንካራ ጎን የተመዘገቡ ተግባራትን አድንቀው፥ ተግባራት እያሉ ሪፖርቶች በተጠናከረ ሁኔታ አለመደራጀት እና በቀበሌያት በቂ ድጋፎች ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ስለምክር ቤት የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር እና ክፍተቶችም እንዲሻሻሉ እየሰሩ እንዳሉና የመሰረተ ልማት ውስንነቶችን ለማሻሻል ጥረቶች መደረጋቸውን የዋና አስተዳዳሪው ልዩ አማካሪ አቶ አያኖ ካወዳይታ ተናግረዋል።
የዞኑ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤን ጨምሮ የዞኑ ምክር ቤት የማናጅመንት አባላት ድጋፍና ክትትሉ እጅግ የሚደግፍ መሆኑን ገልጸው በክፍተት የታዩትን ለማሻሻል እና በጥንካሬ የተመዘገቡትን ለማስቀጠል እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ በድጋፍ እና ክትትሉ መደሰታቸውን ገልጸው ክትትሉ የዘነጋናቸውን ተግባራት እንድንከውን ያነቃን ምልከታ ነው ብለዋል።
የሚሻሻሉ ክፍተቶችን ለማረም ከወዲሁ ዝግጁ መሆናቸውን የተናገሩት ዋና አፌጉባኤው፥ የበጀት እጥረት እና የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ተግባራትን ለማከናወን ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።
መረጃው
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
መጋቢት 23/2016 ዓ/ም







