ርኆቦት የጤና ክብካቤ ሠራተኞች በጎ አድራጎት ማህበር በኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ባአይዴ ጤና ጣቢያ ዘርፈ ብዙ በጎ ተግባራትን አከናውኗል።

ርኆቦት የጤና ክብካቤ ሠራተኞች በጎ አድራጎት ማህበር በኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ባአይዴ ጤና ጣቢያ ዘርፈ ብዙ በጎ ተግባራትን አከናውኗል።

የርኆቦት የጤና ክብካቤ ሠራተኞች በጎ አድራጎት ማህበር ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ኦርካይዶ እንደገለፁት ርኆቦት የጤና ክብካቤ ሠራተኞች በጎ አድራጎት ማህበር ለህብረተሰብ ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ መሆኑን ገልጸዋል።

ርኆቦት የጤና ክብካቤ ሠራተኞች በጎ አድራጎት ማህበሩ ኮንሶን ማዕከል በማድረግ ኮንሶ እና አካባቢውን ከተላላፊ በሽታዎች ለመከላከል በዞኑ ወረዳዎች በሚገኙ የተለያዩ ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም በኮንሶ ማረሚያ ተቋም ተዘዋውረው ዘርፈ ብዙ የጤና አገልግሎቶች እንዲሁም የምግብና አልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸውን አቶ ጴጥሮስ ጠቅሰዋል።

በጎ አድራጎት ማህበሩ በባአይዴ ጤና ጣቢያ ለነብሴ ጡር እናቶች፣ለወላድ እናቶች፣ለአቅሜ ደካሞች እንዲሁም ድጋፍ ለሚሹ አካላት ሙዝ፣ሣሙና፣ውሃ አጋር፣ለስላሳ፣የአልባሳት ጨርቅ ድጋፍ ያደረጉት ሲሆን ለበሽተኞች የፀሎትና የስነ ልቦና ምክር የመስጠት ተግባራትን አከናውነዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች፣የደም ግፊት፣የስኳር በሽታ ምርመራ፣የህክምና አገልግሎት እንዲሁም የእግር አጠባ መርሃ ግብሮች የተከናወኑ ሲሆን በቀጣይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎችን በማዘጋጀት የህብረተሰቡን የጤና ችግር ለመቅረፍ ዕቅድ መያዙንም አቶ ጴጥሮስ አስረድተዋል።

ርኆቦት የጤና ክብካቤ ሠራተኞች በጎ አድራጎት ማህበር ፀሐፊ ዶ/ር ዳንኤል ካማኔ በበኩላቸው የወባ እና ኩፍኝ ወረረሽኞችን ለመከላከል ህብረተሰቡ ነቅቶ በቅድሚያ ከወረረሽኞች ራሱን እንዲከላከሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የደም ግፊትና ስኳር በሽታ ጋር ተያያዞ ከ40 ዕድሜ በላይ ያሉ ሁሉ በየጊዜ ራሳቸውን መመርመር ይኖርባቸዋል ያሉት ሲሆን የጤና ኤክስቴንሽኖች ደግሞ ለተግባሩ ትኩረት በመስጠት ህብረተሰባችንን ከሽታ መከላከል የበኩላችንን ሊንወጣ ይገባል ብለዋል።

የባአይዴ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ኩልቻ ኩንጩርታ በበኩላቸው ርኆቦት የጤና ክብካቤ ሠራተኞች በጎ አድራጎት ማህበር ስላደረገልን በጎ ተግባር ምስጋናችን የላቀ ነው ያሉት ሲሆን ማህበሩ እንዲህ የሚያስመሰግን ተግባር እንዲያደርግልን ያደረገ የዞንና የወረዳው መንግስት ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ ከልብ አመስግነዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት በበኩላቸው ርኆቦት የጤና ክብካቤ ሠራተኞች በጎ አድራጎት ማህበር ፍቅርንና በጎነትን በተግባር የገለፀልን ሲሆን ዛሬ የተደረገልን ዘርፈ ብዙ የጤና አገልግሎት በተጨማሪ መንፈሳችንን ያደስንበትና የህሊና እርካታ ያገኘንበት በመሆኑ ማህበሩ ስላደረገልን ጉብኝት ምስጋናችን የላቀ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በመጨረሻም የበጎ አድራጎት ማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ኦርካይዶ የስራው ስኬት የአስተዋጾኦ ያደረጉ የዞኑ መንግስትን ጨምሮ ሌሎች አካላት ምስጋናቸውን ያቀረቡት ሲሆን የማህበሩ አባላት እና የጤና ጣቢያው ሠራተኞች በጋራ የጽዳት ዘመቻ በማድረግ መርሃግብሩ ተጠናቋል።

መረጃ ከስፍራው በኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ጥቅምት 22/2017 ዓ/ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *