በምግብ ዋስትና ራስን ለመቻል መግባባት፣ ማጥራት፣ ማቀናጀት፣ ማሸጋገር እና ማምረት እንደሚገባ ተገለፀ።

“ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር!” በሚል መሪህ ቃል የዞኑ አመራሮች የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮንሶ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ መሣይ አሰፋ እንደተናገሩት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድነት ቆመው በልማትና በምርታማነት ሉዓላዊነቷን ለትውልድ ማስረከብ እንደሚገባ አስገነዘቡ።

ከዚህ ቀደም ኮንሶ ዞን የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎችን ያስታወሱት አቶ መሣይ፤ ይህ የተረጂነት ታሪክን ለመቀልበስ የዞናችንን ህብረተሰብ በተቀናጀ ልማታዊ ፕሮግራሞች በማሳተፍ በምግብ ዋስትና ራሱን የቻለ ማህበረሰብ ለመፍጠር በትኩረት መስራት ይኖርብናልም ብለዋል።

የኮንሶ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪና የዞኑ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ ጋራ በበኩላቸው ጥንት አባቶች ያወረሱንን የስራ ባህል በማጠናከር የግብርናን ኢኮኖሚ ማስጠበቅ ይገባናል ብለዋል።

አቶ አዲሱ ጨምረው የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ የምንችለው ከድህነት ስንላቀቅ ብቻ በመሆኑ ጠንክሮ በመስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አመራሩ በመፍጠንና በመፍጠር ዕሳቤ የተጀመሩ ልማታዊ መነሳሳቶችን በተጨባጭ ለማስመዝገብ የለውጥ ጉዞ ማጠናከር እንደሚገባ የኮንሶ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ከፈኔ ትጫሮ አሳስበዋል።

አቶ ከፈኔ አክለውም ከተረጂነት ወደ ረጂነት ለመሸጋገርና በምግብ ዋስትና ራስን ለመቻል በቂ ሀብት አለን ያሉት ሲሆን ከተረጂነት የመላቀቅ ግብን ለማሳካት መግባባት፣ ማጥራት፣ ማቀናጀት፣ ማሸጋገር እና ማምረት ይጠበቅብናል ሲሉ አብራርተዋል።

ከተረጂነት መላቀቅ ከራስ አልፎ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ያሉት ሀሳብና አስተያየት ሰጪ ተሳታፊ አመራሮች፤ ከተረጂነት ለመላቀቅ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።

እርስበርስ የመረዳዳት ጥንታዊ ባህላችንን በማጠናከርና ያሉንን ፀጋዎች በሚገባ ተጠቅመን ከተረጂነት ራሳችንን ማላቀቅ ዋነኛ የትግል አጀንዳ በማድረግ ለውጤታማነቱ በቁርጠኝነት መረባረብ ከሁሉም ይጠበቃል ስሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪው አቶ አዲሱ ጋራ አስረድተዋል።

በመጨረሻም የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሣይ አሰፋ በሀገር ደረጃ “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር!” ንቅናቄውን በሁሉም መዋቅሮች እስከ ቀበሌ በማውረድና ሁለንተናዊ ለውጥ በማምጣት ሀገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊረባረቡ ይገባል ስሉ አሳስበዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

ግንቦት 27/2016 ዓ/ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *