የኮንሶ ዞን ሠራተኞች ሠራተኞችና  አመራሮች የጋራ የአቋም መግለጫ

የኮንሶ ዞን ሠራተኞች ሠራተኞችና  አመራሮች የጋራ የአቋም መግለጫ

የኮንሶ ህዝብ በስራ ታታሪነቱ በዓለም ያስመሰከረ ህዝብ ስሆን በተለያዩ አከባቢዎች ግጭቶች ስነሱ በባህሉ የማስታረቅ ልምድ ያለው ታላቅ ህዝብ ነው።

በአሁኑ ጊዜም በጃርሶ ለሃይተና በናላያ ሰገን ታራጋሜ ሕዝብ መካከል የተከሰተው ችግር የኮንሶን ህዝብ የማይወክል ማንንም ልኮንነው የምገባ ተግባሪ መሆኑን፤ እኛ የኮንስ ዞን የመንግስት ሠራተኞች እና አመራሮች ዛሬ ማክሰኞ 13/09/2016 ዓ.ም  በጋራ ባደረግነው ወይይት በመግባባት የምከተሉትን ባለ ሰባት ነጥቦች የአቋም መግለጫ አውጥተናል።

  • 1.   በጃርሶ ለሐይቴና በናላያ ሰገን ታራጋሜ ሕዝብ መካከል የተከሰተዉ ግጭት የኮንሶ ባህልና እሴት የናዳ እንዲሁም የኮንሶ ህዝብ የማይወክል በመሆኑ እኛ የኮንሶ ዞን ማዕከል ፓብሊክ ሰርቫንትና አመራሮች ተግባሩን በአጽኖት  እናወግዛለን!
  • 2.  በጃርሶ ለሐይቴና በናላያ ሰገን ታራጋሜ ሕዝብ መካከል የተከሰተዉ ግጭት  መንስኤ የሆኑት እንዲሁም አንድ ቤተሰብ በሆነ ህዝብ መካከል  አለመግባባት በመፍጠር  ለንብረት  ዉድመት  ምክንያት  የሆኑ አካላት ጥንቃቄ  በተሞላበት  አኳሃን ተጠርጣሪዎችን ለሕግ  እንዲቀርቡ እንጠይቃለን!
  • 3.  የተከሰተዉ ግጭት ዳግም እንዳያገረሽ ከምንጩ ለማድረቅና የህገዝብ ለህዝብ ግኑኝነት እንድጠናከር ወንድም እህት የነበረው የህብረተሰባችን ባህል ያከበረ እና ያጠናከረ እንድሁም እንዲንረዳዳ የማቀራረብ  ስራን ለመስራት የበኩላችንን አስተዋጽኦ  ለማበርከት ቃል እንገባለን!
  • 4.  በማህበራውዊ ሚዲያ የጥላቻ ንግግሮችና የኮንሶን ገጽታ የሚያጠለሹ፣ በወንድሞች መካከል መጠራጠርና አለመግባባትን የሚፈጥሩ ግለሰቦች በጥብቅ እያወገዝን ችግሮች ካሉ በመቀራራብ ለመፍታት ቃል እንገባለን!
  • 5 ግጭቶች ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት አዝማሚያ በመገምገም የግጭቱ ቀድሜ ትንተና በማድረግ እንድሁም ህዝቡን ለማወያየትና የመከልከል ስራን ለመስራት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን!
  • 6 በአጎራባች ዞኖች መካከል በየጊዜው የሚከሰቱ የዝርፊያ እና ህይወት የማጥፋት እና በኮንሶ ዞን ውስጥ በህዝቡ መካከል ተሰውረው በእኩይ ተግባር የተሰማሩ ዘራፊዎች እና የግጭቱ ጠማቅዎች እንድሁም ወንበዴዎች ለህግ እንዲቀርቡ ከወንድም  ኧሌ ህዝብ ጋር ለመስራት ቃል እንገባለን!
  • 7 በአሁኑ ጊዜ የወደሙ ንብረት አውዳሚው አካል ራሱ እንድተካ የተደረግው የመንግሥት አቅጣጫ እየደገፍን በቀጣይ ይህንን አሰራር ህግ ሆኖ እንድጸድቅ ለኮንሶ ዞን ም/ቤት እንድቀርብ አበክረን እንጠይቃለን!

መረጃ
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
                 ግንቦት 13/2016ዓ.ም

Giya Gina

IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

Related Posts

በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *