የመንግስት ውስን ሃብት በተሰጠው ኃላፊነትና አሰራር መሠረት ከብክነት በመከላከል ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባ ተጠቆመ።

#Ethio_Konso የኮንሶ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሞ በ2016 ዞናዊ ቅድመ በጀት ዝግጅት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።

በግምገማ መድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮንሶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሣሁን ካርሻዎ እንደተናገሩት የፋይናንስ አሠራሮችን በጊዜ በመገምገምና ለክፍተቶች መፍትሄዎችን ማመንጨት ለስኬት መንገድ ማበጀት እንደሆነ ገልጸዋል።

እንደ ክፍተት የታዩ የበጀት እጥረት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተሸጋግሮ የመጣው የአፈር ማዳበሪያና ጡረታ ዕዳዎችን እስከ ታችኛው መዋቅር ወርደው መገምገማቸውንና እነዚህ ጉድለቶች የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳይፈጥሩ ከድህነት ቅናሽ ሴክተር መ/ቤቶች ጋር በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን አቶ ካሣሁን አብራርተዋል።

በቀጣይ በ2016 በጀት ዓመት ጉድለቶች ዳግም እንዳይከሰቱ የውስጥ ገቢን አሟጦ መሰብሰብ፣ ባለዕዳዎችን በወቅቱ ለይቶ በህግ ለማየት ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን አቶ ካሳሁን አብራርተዋል።

የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ኩሴ ነጋሽ በበኩላቸው ያጋጠሙን የበጀት እጥረትና የጥሬ ገንዘብ ችግርን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድረሻ አካላት ያሳተፈ ሀብት አሰባሰብና ቁጥጥር እንደሚገባም ጠቁመዋል።

አቶ ኩሴ ጨምረው የገቢ አሰባሰብ አቅምን ለማጠናከር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ርብርብን የሚጠይቅ በመሆኑ በጋራ ሰርተን ክፍተቶችን በመሸፈን የሚናገለግለው ህዝብን ማሻገር ያስፈልጋልም ብለዋል።

የኮንሶ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ገልገሎ ገልሾ በመድረኩ እንደገለፁት በፋይናንስ አሠራር ግልፀኝነትን በመፍጠር መመሪያዎችን መሠረት ያደረገ አሰራሩ ልጠናከር ይገባል ብለዋል።

በኦዲት የሚገኙ ሃብቶችን ወደ ገንዘብ ለመቀየር ፋይናንስ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ያሉት አቶ ገልገሎ ተቋሙ በአሰራር መመሪያው መሠረት በህግ ማዕቀፍ ሊመራና ጠንካራ የሆነ የውስጥ ቁጥጥር ለመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

የፋይናንስ አሰራር ስርዓቱን ጠብቆ በመመሪያው መሠረት ካልተሰራ በበጀት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር መሆኑና የጥሬ ገንዘብ ዕጥረት፣ በስታንዳርዱ መሠረት ገቢን አሟጦ ያለመሰብሰብ፣ ከዓመት ዓመት የሚሸጋገር የደመወዝ ብድር፣ ተሰብሳቢና ተከፋይ ገንዘብ ክምችት በክልሉ የኢንቨስትመንት ፕሮግራም ፋይናንስ ከፍተኛ የሂሳብ ባለሙያ አቶ ካማሣ ገለቦ የ9 ወራት አፈፃፀም ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት አመልክተዋል።

የሠራተኛ ሌጀሮችን በወቅቱ ማዘጋጀትና ማደራጀት፣ ሴክተር መ/ቤቶችና ፋይናንስ በቅንጅት በመስራት የታዩ ጉድለቶችን በመቅረፍ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባ አቶ ካማሣ አብራርተዋል።

ሀሳብ አስተያየታቸውን ከሰጡት ተሳታፊዎች መካከል የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሄኖክ በየኔ እንደገለፁት በዞን ደረጃ የማዘጋጃ፣ የጤና እንዲሁም የትምህርት ቤቶች ገቢ በሚገባ ያለመሰብሰብ ጉድለቶች መኖራቸውን ገልፀው ከዚህ በተጨማሪ የፋይናንስና የገቢ ሴክተር የገቢ ምዝገባ መረጃ ተዓማኒና ተመሳሳይ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ በቀላሉ የሚታይ ጉዳይ አይደለም ያሉት የከና ወረዳ እና የካራት ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች ከማዳበሪያ ሽያጭ ደረሰኝ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከዞን እስከ ክልል ቅንጂታዊ አሰራር እንደሚያስፈልግ በአስተያየት ተደምጠዋል።

በመድረኩ የካራት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ገለቦ የ2016 ቅድሜ ዕቅድ ዝግጅት ተሞክሮ አቅርበዋል።

በዞኑ ምክር ቤት የበጀት ፋይናንስና የመንግስት ኃብት ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አያኖ ካውዳይታ በበኩላቸው በዘጠኝ ወራት የተስተዋሉ ጠንካራ ጎኖችን አድንቀው የተስተዋሉ ክፍተነለቶችን በቅንጅት ለመፍታት መረባረብ እንደሚገባቸው አስታውቀዋል።

በመድረኩ የሁሉም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋም ኃላፊዎች፣ ልማት ዕቅዶች፣ ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት፣ ድህነት ቀናሽ ሴክተሮችና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

መረጃው

የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

ሚያዝያ 25/2015 ዓ/ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *