የኮንሶ ሳብስቴሽን ፕሮጀክት፤ የግንባታ ቦታ ምልከታና የቴክኒክ ማረጋገጫ ሥራ ተካሄደ፣

የኮንሶ ሳብስቴሽን ፕሮጀክት፤ የግንባታ ቦታ ምልከታና የቴክኒክ ማረጋገጫ ሥራ ተካሄደ፣

ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም ( ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጅነሪንግ ክፍል የተውጣጣ የኃላፊዎችና የባለሙያዎች ቡድን በኮንሶ ዞን ለሚገነባው የሳብስቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ቦታ ምልከታ፣ የዲዛይንና የሳይት መረጃ ማረጋገጥ እንዲሁም ቀሪ የሰርቬይንግ ሥራዎችን ለማከናወን ኮንሶ ዞን ገብቷል።

ቡድኑ ወደ ኮንሶ ዞን ሲገባም የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ በቢሮአቸው ተቀብለው ከቡድኑ አባላት ጋር የፕሮጀክቱን የአሁኑን ሁኔታና በቀጣይ ሊከናወኑ ስለሚገባቸው ሥራዎች ተወያይተዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በዚህ ወቅት የኮንሶ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ የሆነውን የኤሌክትሪክ ችግር ለመፍታት መንግስት እያከናወነ ላለው የተለያዩ ጥረቶች ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ገለቦ ጎልቶሞ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ለህዝቡ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ትኩረት በመስጠት እስከ ኮንሶ ድረስ መጥተው የፕሮጀክቱን ሁኔታ በመመልከታቸው በኮንሶ ህዝብ ስም አመስግነዋል።

በተጨማሪም በዞኑ የሚታየው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገቱ ላይ እያሳደረ ስላለው አሉታዊ ተፅዕኖ ለቡድኑ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በውይይቱ ላይ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጅነሪንግ ክፍል የመጡት የቡድኑ ኃላፊ አቶ አስመራ ጋዲሳ እና አቶ ወንድወሰን እጅጉ እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የቡድኑ ኃላፊ አቶ አስመራ ጋዲሳ በበኩላቸው፣ የዞኑ አመራር ለፕሮጀክቱ እያሳየ ያለውን ትኩረትና የሚሰጠውን አቅጣጫ አድንቀዋል። ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ተደጋጋሚ የቴክኒክ ምልከታና ሥራ ሊያስፈልግ እንደሚችል ገልጸው፣ የዞኑ አመራር የሚያደርገው ትብብርና ድጋፍ ለሥራው ስኬት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለሙያዎቹ በተጨማሪም የሳብስቴሽኑ ግንባታ ወቅት ትላልቅ ዕቃዎችና መሳሪያዎች ወደ ቦታው ሲጓጓዙ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች፣ የመሠረት ሁኔታ፣ የቦታው አቀማመጥና ሌሎች የቴክኒክ ጉዳዮች በተገቢው መጠናታቸውን አስረድተዋል።

የሰርቬይንግ ባለሙያው አቶ ደንድር ግርማ እንደገለጹት፣ የሳይት ምልከታው ዋና ዓላማ የሳብስቴሽኑ ግንባታ ቦታ ከካራት ከተማ ጋር ያለውን ርቀትና የመዳረሻ ሁኔታ መገምገም ነው።

በተለይም ወደ ግንባታ ቦታው ትላልቅ የሳብስቴሽን መሳሪያዎች ሲጓጓዙ አስቸጋሪ መንገዶች፣ ወንዞች፣ ድልድዮች ወይም ሌሎች መሰናክሎች እንዳያጋጥሙ የመዳረሻ መንገዱ በዝርዝር መገምገሙን ገልጸዋል።

እንዲሁም በቀጣይ የፕሮጀክቱን ግንባታ የሚያከናውኑ ሠራተኞች በአካባቢው ሲኖሩ ለመኖሪያና ለሥራ ምቹ ሁኔታ መኖሩን ለማረጋገጥም ምልከታ መደረጉን አስረድተዋል።

በቦታው የተገኙ የዞኑ ኃላፊዎችና የካራት ከተማ አመራሮች በበኩላቸው፣ የግንባታ ቦታው ከከተማው ውጭ መገኘቱ ለፕሮጀክቱ ተጨማሪ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። ከተማዋ ወደፊት በዚህ አቅጣጫ የምታስፋፋ በመሆኗ፣ ቦታው በዞኑ የወደፊት የእድገት አቅጣጫ ውስጥ የሚገኝ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጨማሪም በአካባቢው በቀጣይ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችና ሌሎች የልማት ተግባራት ሊከናወኑ እንደሚችሉ በመጠቆም፣ የሳብስቴሽኑ ፕሮጀክት ለዞኑ የወደፊት የኢኮኖሚና የኢንዱስትሪ እድገት የሚኖረውን ሚና አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጅነሪንግ ቡድኑ በሁለት ቡድን ተከፍሎ የተለያዩ የቴክኒክና የሳይት ምልከታዎችን እያከናወነ ሲሆን፣ የቀሩ የሰርቬይንግና ሌሎች የቴክኒክ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ የፕሮጀክቱ ምዕራፍ ለመሸጋገር እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

የኮንሶ ሳብስቴሽን ፕሮጀክቱ በዞኑ የሚታየውን የኃይል አቅርቦትና የመቆራረጥ ችግር በማቃለል፣ በአካባቢው የኢኮኖሚ፣ የኢንዱስትሪና የማህበራዊ ልማት እንቅስቃሴዎችን ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በጊያ ግና

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ

    በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር ሽሚድ የተመራ ልዑክ ቡድን ኮንሶ ዞን ገባ ካራት፦ ሕዳር 3/2019 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) በHEKS-EPER ዓለም አቀፍ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዋልተር…

    ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት

    የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች “ኮሙኒኬሽን ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ቃል በ100 ቀናት ዕቅድና በቀጣይ ተግባራት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የ100 ቀናት ዕቅድ እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *