ፓርቲው የ100 ቀናት ልዩ ልዩ ተግባራት እቅድ አፈፃፀምና የአመራር ስምርትን ገመገመ።
የአመራር ስምርት ግምገማ የመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ እና የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻካይቶ ሳይሙሮ እንደተናገሩት በትኩረት ለውጤት በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።
በትምህርት፣ በግብርና፣ በጤና፣ በንግድና ገበያ፣ በሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀት፣ አንድ ተራራ ማልማት፣ ስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም በሌሎች ተግባራት ዙሪያ የተከወኑ የአመራር ስምርት ሪፖርት አድምጠዋል።
የሁሉም ወረዳ ስምርት ጠርናፊ አመራር እንደተናገሩት “አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ” ንቅናቄን በማጠናከር መንግስት ሰራተኞች፣ ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች እና ከተማና ቀበሌ ነዋሪዎች ድጋፉን እንዲያደርጉ በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ልዩ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ተግባራትን አቅደን እየሰራን ነው ያሉት የካራት ከተማ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አማኑኤል ገርሞ አመራሩ ታች ወርዶ በቀጥታ ከህዝቡ ጋር በመገናኘት ለውጤት እየሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።
አመራሩ በካራት ከተማ፣ ካራት ዙሪያ፣ ሠገን ዙሪያ፣ ከና እና በኮልሜ ወረዳ ስምርት በመውሰድ ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች እና በ100 ቀናት የእቅድ ተግባር አፈፃፀም ሂደቱን እየሰሩ መሆናቸውን በሪፓርቱ ተደምጧል።
የተጀመሩ መደበኛ ገቢ አሰባሰብ፣ የተማሪ መፅሐፍት ግዥ ገቢ፣ ሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀት፣ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት እና የፓርቲ ገቢ አሰባሰብ ስራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
የኮንሶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻካይቶ ሳይሙሮ “አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ” ገቢ ማሰባሰቢያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር መከፈቱን ተናግረው ተማሪ ልጆቻችን በመጽሐፍ እጦት ምክንያት በትምህርት ገበታቸው ውድቀት እንዳይገጥማቸው ለመፅሐፍት ግዥ ለሚሆን ገቢ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገልገሎ ገልሾ በማጠቃለያ ንግግራቸው የፓርቲና መደበኛ ገቢን አሟጦ መሰብሰብ፣ ለመማሪያ መጽሐፍት ገቢ አሰባሰብን ለውጤት መስራት፣ የእርሻ ተግባራትን ማጠናከር፣ በጤና ዘርፍ ያሉና ሌሎች የስምርቱ ሁለንተናዊ ተግባራትን አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲሰራቸው አሳስበዋል።
በዞን ዋና አስተዳደሩና በፓርቲ ኃላፊው የተመራው ግምገማ መድረኩ የዞን ምድብተኛ አመራር እና የወረዳዎች የፊት አመራሮችን ያሳተፈ ነበር።
መረጃ
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
ሚያዚያ 08/2016 ዓ.ም







