በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ጉባኤን ለማካሄድ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ምክር ቤት ጉባአኤው ልዩ ልዩ አጀንዳዎችን ለምክር ቤቱ አቅርቦ ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።


የኮልሜ ወረዳ ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ሚያዚያ 11-12/2016 ዓ/ም እንደሚካሄድ የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገቢኖ ጎርቶሎ አስታወቁ።

ምክር ቤቱ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ሲያካሂድ የምክር ቤት፣ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች እና ፍርድ ቤት የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ምክር ቤቱ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ዙሪያ መክሮ እንደሚያፀድቅ የተናገሩት ዋና አፌ ጉባኤው አቶ ገቢኖ የተሻሻለው የበጀት ረቂቅ አዋጅ፣ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች ሹመትና የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሹመት ምክር ቤት አባላቱ መርምሮ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

ለጉባኤው ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችን፣ የምክር ቤቱ አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች በተባለው ዕለት 2:30 ኮልሜ ከተማ ትምህርት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲትገኙ ምክር ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሚያዚያ 09/2016 ዓ.ም

  • Giya Gina

    IS Ethiopian computer engineering graduate, journalist, and photographer who creates content focused on informing and inspiring local audiences. You can explore a portfolio of technical skills and projects on the Website. https://giyagina.22web.org

    Related Posts

    ደቡብ ኢትዮጵያ

    ደቡብ ኢትዮጵያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን በውብ የባህል ቀለም እና እሴት ደምቃ ተቀብላቸዋለች!#PMOEthiopia

    በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣

    አመራራችን ችግሮችን ወይም ፈተናዎችን ወደ ምቹ አጋጣሚ በመቀየሮ ለለውጥ የሚሰለፍ መሆን አለበት:- ኮሚሽነር ሐልገዮ ጅሎ ‎በኮንሶ ዞን ያሉ አጠቃላይ አመራሮች በወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፣ ‎”የአሜሪካ-እስራኤል እና…

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *