ዋና አስተዳደሩ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ይህ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች መንፈሳዊ ትርጉም ያለው በመሆኑና የረመዳን ወር ማጠቃለያ ታላቅ በዓል በመሆኑ መላው ህዝቤ ሙስሊም እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን! ብለዋል፡፡
በአንድ ወር የረመዳን ፆም ቆይታ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህደት ውስጥ የእምነቱ ተከታዮች ለነበራቸው ቆይታ ፈጣሪ ብርታቱን ሰጥቶ ለበዓሉ ሲትበቁ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ፣ ወገኖችን በመርዳትና በማገዝ ዒድ አል ፈጥርን እንዲያሳልፉ ሲሉ አቶ ገልገሎ ተመኝተዋል።
የረመዳን ወር በመላው ሙስሊሙ ማህበረሰብ በናፍቆት የሚጠብቅ፣ በወሩ የጄነት በሮች የሚከፈቱበት፥ ሙስሊሙ በፆምና በኢባዳ ከፈጣሪው ጋር የሚቀራረቡበት፣ ዚክር የሚበዛበት፣ በጎነት የሚንሰራፈበት፣ የምህረትና የመባረክ ወር በመሆኑ ለህዝቤ ሙስሊሙ ታሪካዊ ወር ነው ብለዋል።
የዘንድሮ የረመዳን ፆም ወቅት ባልተለመደ መልኩ የዞኑ መንግስት ለህዝቤ ሙስሊሙ የአፍጥር ስጦታ በማድረግ ቤተሰባዊ አጋርነትን የገለፀበት የፆም ወቅት ሲሆን ለወደፊት በመቀጠል የሀይማኖት ብዝሀነታችንን በመተሳሰብና በመከባበር የሚንሰራ ይሆናል ብለዋል።
የወጣቱን ስብዕና በመገንባት፣ በሰው ኃይል የበለፀገች እና ለሀገራዊ ለውጥ የሚተጋ ወጣት ማፍራት እንዲቻል በኮንሶ ዞን የእስልምና እምነት መሪዎች አደራ እንዲወጡም ጭምር ዋና አስተዳደሩ አቶ ገልገሎ ጠይቀዋል።
በመጨረሻም እንኳን ለ1 ሺህ 445 ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት ዋና አስተዳደሩ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
መረጃ
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ሚያዚያ 01/2016 ዓ.ም







